ቻይና ውስጥ የመኪና አሽከርካሪ 35 ሰዎች ገጭቶ ገደለ
ዙሃይ በተባለች የደቡባዊ ቻይና ከተማ አንድ የመኪና አሽከርካሪ በስፖርት ማዕከል ስፖርት ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች መሃል መኪናውን እየነዳ ገብቶ 35 ሰዎችን ሲገድል ሌሎች 43 ሰዎች ማቁሰሉን ፖሊስ አስታወቀ። የስድሳ ሁለት ዓመቱ የመኪናው አሽከርካሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ ትላንት ሰኞ ማታ አስታውቋል። ድርጊቱ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ጥቃት ወይም አደጋ ይሁን ለጊዜው አለመታወቁን ፖሊስ አመልክቷል። ድርጊቱ የተፈጸመው ከተማዋ በየዓመቱ የቻይና ህዝባዊ ነጻ አውጪ ሠራዊት የአቪየሽን ትርዒት የምታስተናግድ ስትሆን ትርዒቱ ዛሬ ማክሰኞ ተከፍቷል።
What's Your Reaction?