የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ ከታየው የሞባይል ስልክ ስርቆት በሰላም ተጠናቆዋል
የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሞባይል ስልክ ስርቆት መፈፀም እና አልፎ አልፎ ከተከሰቱ ቀላል የመወደቅ አደጋ በስተቀረ በሰላም ተጠናቆዋል
የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሞባይል ስልክ ስርቆት መፈፀም እና አልፎ አልፎ ከተከሰቱ ቀላል የመወደቅ አደጋ በስተቀረ በሰላም ተጠናቆዋል
ድንቅ ነሽ በሚል የሰው ዘር መሰረት በሆነችው ሉሲ የተሰየመው የዘንድሮው የ 10 ኬ ሩጫ 24ኛው ታላቁ ሩጫ በርካቶች በ አዲሰ አበባ የተካፈሉበት ነበር።
በታላቁ እሩጫ በተደጋጋሚ በተለይ የውሀ መርጫዎቹ አካባቢ የሰልክ ስርቆት ተፈፅሞዋል ከመፈፀሙ በስተቀር የታየ የፅትታ ችግር አልነበረም በሩጫ ተካፋይ የነበሩ ወጣቶች ዘንድ በአብዛኛው የ አብዱ ኪያር ‘ትልቅ ፈጣሪነው የሰው ትልቅ የለም ‘ የሚለው ሙዚቃ ሲዘፈን ተደምጥዋል ።
የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ ውድድር ከ50ሺ በላይ ተሳታፊዎችን ከ20 በላይ የተለያዩ ሃገራት የመጡበት 500 በላይ የጤና ሯጮች እና ታዋቂ አትሌቶች ተካፈለውበታል ።
በርካታ ዜጎች የተሳተፉበት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ተቀናጅቶ የሩጫው ተሳታፊዎች ደኅንነት ተጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ የድርሻውን መወጣቱ ተገልጿል፡፡
ታላቁ ሩጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ አካላት ትብብር ላደረጉት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፣ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት አካላትም የፌደራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡
What's Your Reaction?