ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎትን በደቡብ ምስራቅ ሪጅን ቢሾፍቱ ከተማ አስጀመረ 

ኢትዮ ቴሌኮም ,የአምስተኛው ትውልድ, 5ጂ, የሞባይል አገልግሎትን በደቡብ ምስራቅ ሪጅን ቢሾፍቱ ከተማ አስጀመረ 

Nov 14, 2024 - 10:09
 0  25
ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎትን በደቡብ ምስራቅ ሪጅን ቢሾፍቱ ከተማ አስጀመረ 

ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎትን በደቡብ ምስራቅ ሪጅን ቢሾፍቱ ከተማ አስጀመረ 

ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ምስራቅ ሪጂን ቢሾፍቱ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጣቢያዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ በከተማዋ እና አካባቢው አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡ 

በቢሾፍቱ ከተማ ኩሪፍቱ ዎተር ፓርክ አካባቢዎች፣ በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን፣ ሰንሻይን አካባቢ፣ ግራር ሜዳ እና የረር የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበር አካባቢ የሚገኙ የድርጅት እና ግለሰብ ደንበኞቹን የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ አድርጓል፡፡ 

የ5ኛው ትውልድ ቴክኖሎጂ እስከ 10 ጊ.ባ በሰከንድ (Gbs) የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ዓለማችን የደረሰበት ዘመናዊ የገመድ አልባ ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ሲሆን፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን እጅግ በላቀ ሁኔታ በመቀነስ (Ultra-low latency) ረገድ ወደ 1ሚሊ ሰከንድ የሚያደርስ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ 

አገልግሎቱ በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር ውስጥ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ በርካታ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን እርስ በርሳቸው ለማገናኘት የሚያስችል ሲሆን፣ የአገልግሎቱ ተግባራዊ መሆን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣውን የደንበኞች የዳታ እና ኢንተርኔት ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የዓለማችን የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆነውን የአምስተኛውን ትውልድ የሞባይል አገልግሎት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂግጂጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና እና አርባ ምንጭ ከተሞች እና አካባቢያቸው ተግባራዊ አድርጓል፡፡ 

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow