ኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነትን ለማክበር ቃል እንድትገባ ሲፒጄ ጠየቀ 

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሀገሪቱ የፕሬስ ነጻነት ይዞታዎቿን እንድታሻሽል እና ለጋዜጠኞች ደህንነት ዋስትና እንድትሰጥ የቀረቡላትን ምክረ ሀሳቦች ዛሬ እየተካሂደ ባለው የተባበሩት መንግስታት ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ግምገማ ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሲፒጄ ጥሪ አቀረበ። የተ መ ድ የሰብዓዊ መብቶች ካውንሲል የኢትዮጲያ አጠቃላይ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ላይ የሚያተኩረው ግምገማ በዛሬው እለት እየተካሂደ ሲሆን ሲ ፒ ጄ እ አ አ የ2019 የፕሬስ ነጻነት እና የጋዜጠኞች ደህንነት ይዞታዋን የገመገመበትን ሪፖርቱን አስቀድሞ ለምክር ቤቱ አስገብቷል። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ግምገማ የሀገራትን የሰብዐዊ መብት ሬኮርድ የሚገመግም ሲሆን ሀገራት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎቻቸውን በተሻለ ለመወጣት እንዲችሉ የቀረቡ ሃሳቦችን ያጤናል። ሲፒጄ ለመንግሥታቱ ድርጅት ያቀረበው ሪፖርት በኢትዮጲያ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ የዘፈቀደ እስር፥ አካላዊ ጥቃት እና ወከባ እንዲሁም እጅግ ጥብቅ የሆኑ የህግ ገደቦች በሚመለከት ዘርዝሯል። ሲፒጄ በሪፖርቱ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ፥ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ምርመራ እንዲካሄድ፥ ጥቃት አድራሾች በተጠያቂነት እንደሚያዙ እንዲረጋገጥ የሚሉ ምክረ ሃሳቦች አቅርቧል። አፋኝ የሆኑ ህግጋት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ደረጃ በሚያከብር መልኩ እንዲሻሻሉ ሲልም አሳስቧል።

Nov 13, 2024 - 13:15
 0  22

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow