ከኢትዮጵያ ለመውጣት የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ኤርትራውያን ገለጹ
በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን፣ የመውጫ ቪዛ ለማግኘት የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ገለጹ። ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ኤርትራውያን፣ ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ፣ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4 ሺህ ዶላር ድረስ እንደሚጠየቁ ገልጸዋል፡፡ የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው ጠይቀዋል፡፡ የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ፣ እየተጠየቀ ያለው ክፍያ፣ ለመውጫ ቪዛ ሳይሆን፣ በሕገወጥ መንገድ ለቆዩበት ጊዜ የሚወሰን ቅጣት ነው ብሏል፡፡ በህገወጥ መንገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በተቋሙ ተመዝግበው ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ እንዲይዙም ጠይቋል፡፡ (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ)
What's Your Reaction?