የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች መካከለኛው ምሥራቅ ገቡ
ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ ከፈጸመችው ዛቻ አንድ ቀን በኋላ ትላንት ቅዳሜ የአሜሪካ ቢ-52 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ መድረሳቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ጦር አስታውቋል። የመካከለኛው ምሥራቅ አና አካባቢው የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ እዝ “ፈንጂ ጣይ አውሮፕላኖቹ ከሚኖ የአየር ኃይል አምስተኛ ክንፍ ደርሰዋል” በማለት በማኅበራዊ ድረገጹ ላይ አስፍሯል። የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሜጀር ጄኔራል ፓት ራይደር “ኢራን፣ አጋሮቿ ወይም በአካባቢቢዎቿ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አሜሪካዊያንን ሰራተኞችን ወይም ፍላጎቶችን ለማጥቃት ይህንን ወቅት ይጠቀሙበታል” ያሉ ሲሆን አይይዘውም “ዩናይትድ ስቴትስ ህዝቦቿን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ትወስዳለች” ብለዋል ።
What's Your Reaction?