የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ ማናቸው?
የሪፐብሊካኑ እጩ ምክትል ፕሬዘዳንት ተወዳዳሪ ጄዲ ቫንስ የሕይወት ታሪክ “የአንድ የትንሽ ከተማ ብላቴና መልካም ሲገጥመው” የሚለውን ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ጄዲ በተራራማው አፓላችን ነው ያደጉት፤ በኋላም አይቪ ሊግ ተብለው ከሚታወቁት ልዩ የሆነ ክብር ካላቸው ዩኒቨርስቲዎች መካከል በዬል ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በዬል የህግ ትምህርት ቤት ቆይታቸውም ከአሁኗ ባለቤታቸው ኡሻ ቺሉኩሪ ጋር ሊተዋወቁ ችለዋል፡፡ ጄዲ ቫንስ ውልደታቸው በሚድል ታውን ኦሃዮ ቢሆንም፤ ነገር ግን ቤቴ ብለው የሚጠሩት ጃክሰን ኬንተኪን ነው፡፡ በልጅነት ህይወታቸው ብሎም በአስተሳሰባቸው ላይ ሚማው ብለው የሚጠሯቸው ሴት አያታቸው ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ የጄዲ ቫንስ የመጀመሪያ እውቅና የመነጨው በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 በታተመው የአሜሪካ የሰራተኛውን መደብ ሕይወት በሚያስቃኘው ‘ሂልቢሊ ኤልጊ’ ብለው በጻፉት እና በኋላም ወደ ፊልምነት በተቀየረው መጽሓፋቸው ነው፡፡ በፖለቲካ ርዕዮተ ዓለማቸው ቀድሞ ትራምፕን ያወግዙ የነበሩት ጄዲ ቫንስ አሁን ላይ የትግል አጋራቸው በመሆን የጎሮጎርሳዊያኑ 2024 ምርጫን ለማሸነፍ እየሰሩ ነው፡፡ መጭው የአውሮፓውያኑ ኅዳር አምስት በሚድረገው ምርጫ ካሸነፉም በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ወጣት ከሆኑ ምክትል ፕሬዘዳንቶች መካከል አንዱ በመሆን በታሪክ ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡ የአሜሪካ ድምጿ ከፍተኛ ዘጋቢ ኬሮላይን ፔርሱቲን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
What's Your Reaction?