የወሮበሎች ሁከት የተባባሰባት  ሄይቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተዘጋ

ሄይቲ ውስጥ ወሮበሎች ትላንት ሰኞ ዋና ከተማዋ ፖርት ኦ ፕሪንስ አውሮፕላን ጣቢያ በማረፍ ላይ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ላይ መተኮሳቸውን ተከትሎ የአውሮፕላን ጣቢያው ተዘግቷል።  በአውሮፕላኑ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው የአዲሱ የሽግግር ጠቅላይ ሚንስትር ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ሲሆን ጥቃቱን ተከትሎ አንዳንድ አየር መንገዶች በጊዚያዊነት  የሄይቲ  በረራዎቻቸውን አቋርጠዋል።  በሌሎች የዋና ከተማዋ አካባቢዎች በታጠቁ ወሮበሎች እና በፖሊሶች መካከል ተኩስ የተካሄደ ሲሆን ወሮበሎቹ ባለጸጎች በሚኖሩበት የከተማዋ አካባቢ  መኖሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።   

Nov 13, 2024 - 13:15
 0  24

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow