"ለምን ይመርጣሉ?" የኢትዮጵያ - አሜሪካውያን ድምጽ
ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ነገ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሁለቱ ዕጩ ተፎካካሪዎች አንዳቸውን ለመምረጥ፣ ለውሳኔያቸው መሰረት የሚያደርጓቸውን ጉዳዮች ይናገራሉ። “በግልም ሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ለውሳኔያችሁ ቅድሚያ የምትሰጡት ምንድነው?” የሚል ጥያቄ ለተለያዩ የማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮች አንስተናል። ሰላምና ፍትሕ ለትግራይ ተወላጆች ዓለም አቀፍ ማኅበር ምክትል ሰብሳቢ አቶ ፒተር ሃጎስ ገብረ ለዚኽና ለሌሎች ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተውናል። አቶ ፒተር እንደ ዜጋ ሕወታቸውን ከሚመለከቱ አበይት ጉዳዮች፣ የተለየ ዋጋ እስከሚሰጧቸው ሌሎች እሴቶች ድረስ ቁልፍ ናቸው የሚሏቸውን ጉዳዮች ያነሳሉ። ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
What's Your Reaction?