ሥለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር
በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ መሠረታዊና ስር የሰደዱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ሀገራዊ መድረክ ነው።
በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ መሠረታዊና ስር የሰደዱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ሀገራዊ መድረክ ነው። ዋና ዓላማው ባለፉት ዓመታት የነበሩ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት፣ ወደ ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት መሻገር ሲሆን ምክክሩን በገለልተኝነት እንዲመራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሠረት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተቋቁሟል። ኮሚሽኑ በዋና ሰብሳቢው በፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮች አሉት።
ኮሚሽኑ ሥራውን በሦስት ዋና ዋና ምዕራፎች ከፍሎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን ሕጎች፣ መመሪያዎችና አደረጃጀቶች የሚሰናዳው በዝግጅት ክፍሉ ሲሆን የሂደት ምዕራፉ ደግሞ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማኅበራት፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከማኅበረሰብ ተወካዮች የተለያዩ አጀንዳዎችን መሰብሰብና ለውይይት የሚሳተፉ ሰዎችን ይመርጣል።
የማጠቃለያው ምዕራፍ በየደረጃው በሚደረጉ ውይይቶች የተደረሱ ስምምነቶችንና የውሳኔ ሐሳቦችን በሰነድ አደራጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብና አፈጻጸማቸውን መከታተል ነው ተቀዳሚ ተግባራቸው።
ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች (አዲስ አበባና ድሬዳዋ) የባለድርሻ አካላትንና የተሳታፊዎችን ልየታ እንዲሁም የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃም የአጀንዳ ማሰባሰብና የምክክር ጉባኤዎች በይፋ መካሄዳቸው ይታወሳል።
ምክክሩ አካታች፣ ግልጽና ገለልተኛ እንዲሆን ከተለያዩ የፖለቲካና የሲቪክ ማኅበራት ሰፊ ጥረትና ግፊቶች እየተደረጉ ሲሆን፣ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ይታመናል።
What's Your Reaction?