የአንጋፋዎቹ ጋዜጠኞች አዲስዓለም ሓድጉ እና በልሁ ተረፈ የምስጋና መርሃ ግብር ተዘጋጀ
በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉት አንጋፋዎቹ የጋዜጠኝነት ሙያ ፈርጦች አዲስዓለም ሓድጉ እና በልሁ ተረፈ በሚዲያ ባለሙያዎችና አድናቂዎቻቸው ሊመሰገኑ ነው
በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉት አንጋፋዎቹ የጋዜጠኝነት ሙያ ፈርጦች አዲስዓለም ሓድጉ እና በልሁ ተረፈ በሚዲያ ባለሙያዎችና አድናቂዎቻቸው ሊመሰገኑ ነው።
"ሰውን በሕይወት ሳለ እንወቅበት፣ እናመስግነው" በሚል መልካም ሀሳብ ላይ የተመሰረተው ይህ የምስጋና መርሃ ግብር፣ ቅዳሜ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በወመዘክር መርስኤሐዘን አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል።
ጋዜጠኛ አዲስዓለም ሓድጉ ትውልዱ በሀገራችን የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ሽሬ አውራጃ ላይ ቆራሮ ወረዳ ነው።
ለ18 ዓመታት በመምህርነት ሙያ ያገለገለ ሲሆን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትግርኛ ክፍል ለ35 ዓመታት ያህል በታማኝነትና በሙያ ፍቅር አገልግሏል።
የጋዜጠኛ በልሁ ተረፈ ደግም በአዲስ አበባ 4 ኪሎ ተወልዶ ያደገ ሲሆን፤ መደበኛ ትምህርቱን አጠናቆ በጋዜጠኝነት ሙያ
በኢትዮጵያ ሬዲዮ ውስጥ በዜና አንባቢነት፣ በፕሮግራም አዘጋጅነትና በዋና ኤዲተርነት ከ37 ዓመታት በላይ የሰራ ጉምቱ ጋዜጠኛ ሲሆን እንደ የወጣቶች ፕሮግራም፣ ከሳይንስ ማህደር እና በእሁድ ጠዋት ፕሮግራም የመሰሉ አየር ላይ የዋሉ ዝግጅቶችን በመምራትና በማዘጋጀት ይታወቃል።
ማንነት ሲፈተሽ እና የአቢሲኒያ ፈርጦች የተሰኙ ሁለት መጻሕፍትንም አሳትሟል።
ይህ ዝግጅት ባለሙያዎቹ ላበረከቱት ሀገራዊ ውለታ ምስጋና ለማቅረብ ብቻ ሳይሆን፣ በኑሮአቸውም ደጋፊና ከጎናቸው የሚቆም የምስጋናና የድጋፍ መድረክ መሆኑ ተገልጿል። ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተከናወነ የሚገኘው ይህ በጎ አደራ፣ ወደፊትም ለሌሎች ባለሙያዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።
What's Your Reaction?