በ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ እለታዊ ምድብ

ሰኔ 17 ሌሊት ላይ የሚደረጉ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ። በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት በአፍሪካው ሀያል ጋና እና በፓናማ መካከል ተጠባባቂ ጨዋታ ይደረጋል።

Jun 17, 2026 - 15:28
 0  3
በ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ እለታዊ ምድብ

ጤና ይስጥልን የሎሚ ስፖርት ተከታታዮች፣ በ2026ቱ የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ማዕቀፍ ውስጥ ዛሬ ሰኔ 17 ሌሊት ላይ የሚደረጉ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ። በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት በአፍሪካው ሀያል ጋና እና በፓናማ መካከል ተጠባባቂ ጨዋታ ይደረጋል።

የአፍሪካውያኑ ጥቁር ከዋክብት  በጠንካራ የአካል ብቃት እና በፍጥነት ላይ በተመሰረተ አጨዋወት ወደ ሜዳ የሚገቡ ሲሆን፣ ተቀናቃኛቸው ፓናማ ደግሞ  በመልሶ ማጥቃት የሚታወቁ በመሆናቸው ጨዋታውን እልህ አስጨራሽ ያደርገዋል። ይህ ጨዋታ በጋና የበላይነት 2 ለ 1 በሆነ ጠባብ ውጤት ይጠናቀቃል የሚል ግምት ሰጥተናል።

#

በሌላ በኩል ንጋት ላይ 11፡00 ሰዓት ላይ የእስያዋ ተስፈኛ ኡዝቤክስታን ከደቡብ አሜሪካዋ ጠንካራ ስብስብ ኮሎምቢያ ጋር ፍልሚያቸውን ያደርጋሉ። በቴክኒክ እና በፈጣን የማጥቃት መስመር የሚታወቁት የኮሎምቢያ ተጫዋቾች ጨዋታውን ለመቆጣጠር የሚጥሩ ቢሆንም በመስመር አጨዋወት የምትታወቀው ኡዝቤክስታን ቀላል ተጋጣሚ እንደማትሆን ይጠበቃል። ይሁን እንጂ የኮሎምቢያ የልምድ ብልጫ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎ ስለሚታመን ጨዋታው በኮሎምቢያ 2 ለ 0 አሸናፊነት ይጠናቀቃል የሚል ግምት አስቀምጠናል።
እናንተስ እነዚህን ጨዋታዎች እንዴት ትገምቷቸዋላችሁ? በትክክል ለገመቱ ተከታታዮቻችን ልዩ ሽልማት አለን። ግምታችሁን እያስቀመጣችሁ የዓለም ዋንጫውን ድምቀት አብራችሁን እንድትካፈሉ ጋበዝናችሁ።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow