የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በታላቅ ጉጉት ተጀመረ!
የዘንድሮው የ2018 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዛሬ ሰኔ 23 ቀን በይፋ መጀመሩን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል!
የዘንድሮው የ2018 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዛሬ ሰኔ 23 ቀን በይፋ መጀመሩን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል! ይህ በመላ ሀገሪቱ የሚጠበቀው አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና እስከ ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም ድረስ በ607 የፈተና ማዕከላት በ6 ዙሮች ይካሄዳል።
አጠቃላይ ተፈታኞች፦ 563,501 ተማሪዎች ለፈተና የሚቀርቡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች 306,456 ተማሪዎች (ከ1ኛ እስከ 3ኛ ዙር)፤ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 257,045 ተማሪዎች (ከ4ኛ እስከ 6ኛ ዙር) ተከፋፍለዉ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል፡፡
የአፈታተን ሁኔታን በተመለከተ በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በ3ኛው ዙር የሚፈተኑ ሲሆን፣ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ በ4ኛው ዙር በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።
ዛሬ ጠዋት የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ያለምንም የትራንስፖርትና የደህንነት ችግር ወደ ፈተና ማዕከላት መግባታቸውንና ፈተናውን በሰላም መጀመራቸውን ተነግርዋል፡ ፡ ተማሪዎችም የተከለከሉ ዕቃዎችን (ስልክ፣ ታብሌት፣ ስማርት ሰዓት ወዘተ) ባለመያዝ ለሕጉ ተገዢ መሆናቸውን አሳይተዋል።
ለተፈታኞች የተሰጠ ማሳሰቢያ
ወደ ፈተና ማዕከል በሚሄዱበት ጊዜ የፈተና መግቢያ ካርድ (Admission Card)፣ የተማሪ መታወቂያ፣ የተፈቀደ እርሳስ፣ ላጲስና መቅረጫ መያዝ ግዴታ ነው። መነጽር የሚያደርጉ ተማሪዎች የሕክምና ማስረጃቸውን መያዝ እንዳለባቸው በጥብቅ ተነግሮል።
ለሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎቻችን በሙሉ መልካም ዕድልና ስኬትን ሎሚ ኒውስ ይመኛል!
#የ12ኛክፍልፈተና #ትምህርት #ብሔራዊፈተና #Ethiopia
What's Your Reaction?