በአሜሪካ የዜግነት መብት ላይ አዲስ ውዝግብ
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህፃናት የትውልድ ዜግነት (Birthright Citizenship) ላይ አዳዲስ ገደቦችን ጣሉ!
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህፃናት የትውልድ ዜግነት (Birthright Citizenship) ላይ አዳዲስ ገደቦችን ጣሉ!
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ምድር ለሚወለዱ ህፃናት የሚሰጠውን አውቶማቲክ የዜግነት መብት ለማገድ እና ለልጅ መውለጃ የሚደረጉ ጉዞዎችን (Birth Tourism) ለመግታት የሚያስችሉ ሁለት አዳዲስ የፕሬዚዳንታዊ ስራ አስፈጻሚ ትእዛዞችን ትላንት ምሽት መፈረማቸው ታውቀል ።
ይህ ውሳኔ የተሰማው የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ የነበረውን አጠቃላይ የትውልድ ዜግነት እገዳ "ህገ-መንግስታዊ አይደለም" ሲል ውድቅ ባደረገ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ነው።
አዲሱ ተዛዝ በቱሪስት ቪዛ ወይም በንግድ ውል ስም ወደ አሜሪካ ገብተው ልጅ በመውለድ ለህፃናቱ አውቶማቲክ የአሜሪካ ዜግነት የሚያስገኙ አሰራሮችን እና ተቋማትን በህግ ለማገድ ያለመ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ ትእዛዝ መሰረት የውጭ ሀገር ሎቢስቶች ፣ የሽብርተኝነት ጥርጣሬ ያለባቸው አካላት እና የውጭ ሀገር መንግስታት ተወካዮች በአሜሪካ የሚያወልዷቸው ህፃናት አውቶማቲክ ዜግነት እንዳያገኙ ይከለክላል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ወደ አሜሪካ የሚገቡ ነፍሰ ጡር ሴቶችን እና የቱሪስት ቪዛ አመልካቾችን በጥብቅ እንዲመረምሩ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል።ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኦቫል ኦፊስ በሰጡት መግለጫ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም፦ "በጠቅላይ ፍርድ ቤት በጣም አሳዛኝ ውሳኔ አስተናግደናል። ሆኖም የሀገራችንን የዜግነት ዋጋ ለመጠበቅ አሁን በሌላ የህግ አሰራር መንገድ ማስተካከያ እያደረግን እንገኛለን" ብለዋል።
ውሳኔው ከተላለፈ ከሰዓታት በኋላ እንደ ACLU (American Civil Liberties Union) ያሉ ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የህግ ባለሙያዎች አዲሱን ትእዛዝ በፍርድ ቤት እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል::
"ህገ-መንግስቱን በስራ አስፈጻሚ ትእዛዝ መቀየር አይቻልም" ያሉት ተሟጋቾቹ የአሜሪካ ህገ-መንግስት 14ኛው ማሻሻያ በሀገሪቱ ምድር ለሚወለድ ማንኛውም ህጻን የዜግነት መብት እንደሚሰጥ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መስጠቱን እና አዲሱ ትእዛዝም እንደቀደመው ውድቅ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ምንጭ፦ White House Press Briefing
ለተጨማሪ እና ለተከታታይ የዜና መረጃዎች ሎሜ ኒውስን (Lomii News) መከታተልዎን ይቀጥሉ!
What's Your Reaction?