በሩሲያ ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቀቀ
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለሩሲያው ኡልያኖቭስክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ-ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለሩሲያው ኡልያኖቭስክ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ-ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ይህ የተቋማቱ ትብብር ተግባራዊ መሆን የቻለው ሁለቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቋንቋ እና በባህል ልውውጥ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የተፈራረሙትን ስምምነት ተከትሎ ነው። ይሄንኑ ስምምነት መነሻ በማድረግ የኡልያኖቭስክ ዩኒቨርሲቲ አማርኛን በተቋሙ ውስጥ ከሚሰጡ የውጭ ቋንቋዎች መካከል አንዱ አድርጎ በሥርዓተ-ትምህርቱ ውስጥ ማካተቱን በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአለቃ ገብረሐና የባህል ጥናት እና ልማት ዳይሬክተር መሠረት ወርቁ ገልጸዋል።
የተደረገው ስምምነት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለሩሲያ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ እንዲያስተምር ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፥ በተመሳሳይ መልኩ ፍላጎት ያላቸው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሩሲያ ቋንቋን እንዲማሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል።
በመጀመሪያ ዙር ስልጠና ከ30 በላይ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህራን በበይነ-መረብ (ኦንላይን) ሲከታተሉት የነበረውን የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት አጠናቀው ተመርቀዋል።
ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አማርኛን ለውጭ ሀገር ዜጎች ለማስተማር የሚያስችለውን ሥርዓተ-ትምህርት አዘጋጅቶ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት አፅድቋል።
በአሁኑ ሰዓትም የሩሲያው ዩኒቨርሲቲ ቋንቋውን የመማር ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች የመመልመል ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
What's Your Reaction?