በደቡብ አፍሪካ ላይ ያለው ውጥረት፤ የፕሬዝዳንቱ አዲስ ጥብቅ እቅድ እና የስደተኞቹ ስጋት

በደቡብ አፍሪካ እየተቀጣጠለ የመጣውን የፀረ-ስደተኞች ተቃውሞ እና የስራ አጥነት  ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ህገ-ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር ያለሙ ጥብቅ አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አድርገዋል። 

Jun 8, 2026 - 14:53
 0  2
በደቡብ አፍሪካ ላይ ያለው ውጥረት፤ የፕሬዝዳንቱ አዲስ ጥብቅ እቅድ እና የስደተኞቹ ስጋት

በደቡብ አፍሪካ እየተቀጣጠለ የመጣውን የፀረ-ስደተኞች ተቃውሞ እና የስራ አጥነት  ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ህገ-ወጥ ስደትን ለመቆጣጠር ያለሙ ጥብቅ አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አድርገዋል። 

እነዚህም ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን የውጭ ዜጎች የሚቀጥሩ አሰሪዎችን ማሰር፣ ለስደተኞች ጉዳይ ፈጣን ውሳኔ የሚሰጡ ልዩ ፍርድ ቤቶችን ማቋቋም እና የማንነት ስርቆትን ለማስቀረት እያንዳንዱን ሰው በባዮሜትሪክ መረጃ መመዝገብ የሚሉ ናቸው።

​ፕሬዝዳንቱ ዜጎች  በህገ ወጥ መንገድ እንዳይወስዱ ቢያስጠነቅቁም፣ የፀረ-ስደተኛ ቡድኖች ግን ህገ-ወጥ ስደተኞች በጥቂት ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ቀነ-ገደብ አስቀምጠዋል። ይህን ተከትሎም በዌስተርን ኬፕ ግዛት በደረሰ ጥቃት የሁለት ሞዛምቢካውያን ህይወት ማለፉን ለአብነት ማንሳት የሚቻል ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችም መኖሪያቸውን ጥለው በማህበረሰብ አዳራሾች፣ ባህር ዳርቻዎችና ተራሮች ላይ ለመጠለል ተገድደዋል። 

በደርባን ከተማም በተመሳሳይ የውጭ ዜጎች ለህይወታቸው በመስጋት ከሀገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮ ውጭ ድንኳን በመጣል ጥገኝነት እየጠየቁ ይገኛሉ። ይህ እየጨመረ የመጣው የጥቃት ስጋት ድንበር ተሻግሮ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ በርካታ ሀገራትም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎቻቸውን በሰላም ለማስወጣት አስቸኳይ ዝግጅት እያደረጉ ነው።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow