ኢትዮጵያ በባህሏ ትደምቃለች፦ ሀገር አቀፍ የባህልና ቋንቋ ሳምንት ተጀመረ
የኢትዮጵያን ብዝኃነትና የጥበብ ቀለም ለዓለም የሚያስተዋውቀውና “የባህል ልማት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የባህልና ቋንቋ ሳምንት በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከፍቷል።
የኢትዮጵያን ብዝኃነትና የጥበብ ቀለም ለዓለም የሚያስተዋውቀውና “የባህል ልማት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የባህልና ቋንቋ ሳምንት በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከፍቷል።
ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች የተወጣጡ ልዑካን፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
ሚኒስትሯ በንግግራቸው፦ “ኢትዮጵያ በብዝኃ ቋንቋና ማንነት የደመቀች ሀገር ናት፤” በማለት፣ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያዊያንን "እኛነት" ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል።
ለአምስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ልዩ ሳምንት፦
የብሔር ብሔረሰቦች ውብ ባህሎችና ቋንቋዎች፣ አይን የሚማርኩ የኪነ-ጥበብና የእደ ጥበብ ውጤቶች፣ የሥነ-ውበት እሴቶችና የኢትዮጵያዊያን መገለጫ የሆኑ ባህላዊ ክህሎቶች ለዕይታ ይቀርባሉ።
ይህ ዝግጅት የሀገሪቱን ብዝኃነት በአንድ መድረክ በማሳየት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከር የራሱን አሻራ ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
What's Your Reaction?