ንቪዲያ ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ለAI መሠረተ ልማት 500 ቢሊዮን ዶላር ሊያሰባስብ ነው

የሴሚኮንዳክተር አምራቹ ንቪዲያ (Nvidia) ለሰው ሰራሽ አስተውሎት AI መሠረተ ልማት የሚውል ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ካፒታል ለማሰባሰብ ከአፖሎ፣ ብላክሮክ፣ ብላክስቶን፣ ብሩክፊልድ፣ ጎልድማን ሳክስ እና ኬኬአር ከተሰኙ ስድስት ግዙፍ የዎል ስትሪት የፋይናንስ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

Aug 11, 2026 - 14:57
 0  6

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁአንግ እንደገለጹት ኢንቪዲያ ከጠቅላላው ገንዘብ እስከ 125 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን ዋስትና የመስጠት አማራጭ አለው።

ይህ አጋርነት የAI አልሚዎች፣ ኩባንያዎች፣ መንግሥታትና የክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች የንቪዲያ ቴክኖሎጂዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በስፋት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የAI ወጪ በዘመኑ ከ730 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይደርሳል ተብሎ በሚጠበቅበት በዚህ ወቅት ለግዙፍ ኢንቨስተሮችም የረጅም ጊዜ የኢንቨስትመንት ዕድል ይፈጥራል።

ይሁን እንጂ የየተቋማቱ ዝርዝር የፋይናንስ አስተዋጽኦ እና ሥራው የሚጀመርበት የጊዜ ሰሌዳ እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow