የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሳምንታዊ ዜና
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንቱን አጠናቆ ዛሬ ወደ አራተኛው ሳምንት ተሸጋግሯል። ያለፈው ሳምንት በሜዳ ላይ ከተመዘገቡ ውጤቶች ባሻገር በሥነ-ምግባር ጉዳዮች ጎልቶ ታይቷል። በተረጋጋ ባህሪያቸው የሚታወቁት የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የ10 ጨዋታዎች ዕገዳ ተጥሎባቸዋል
በሌላ በኩል ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ሲወጣ፣ የኢትዮ ኤሌክትሪኩ አቤል ሀብታሙ በሰብዓዊ ተግባሩ ተመስግኗል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ7 ነጥብ ሊጉን እየመራ ባለበት በዚህ ወቅት የሳምንቱን ዋና ዋና ዜናዎችና የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብርን እንደሚከተለው አቅርበናል።
የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 29 ተጀምሯል። ውድድሩ 18 ክለቦችን በማሳተፍ በሰባት ስታዲየሞችእየተካሄደ ነው፤ እነሱም አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ባህር ዳር፣ አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና እና ሀላባ ናቸው። ጨዋታዎቹበአብዛኛው ከዓርብ እስከ ሰኞ ባሉት ቀናት ይደረጋሉ። ሶስተኛ ሳምንቱን በያዘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱን ክስተቶች እንደዚሁም የዚህ ሳምንት ጨዋታዎችን እነሆ
የሊጉ የውድድርና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ በወላይታ ድቻው ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ላይ የ10 ጨዋታዎች ዕገዳና የ10,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ጥሏል። ቅጣቱ የተጣለው በ3ኛ ሳምንት ወላይታ ድቻ በሀላባ ስታዲየም በባህር ዳር ከተማ 3 ለ 1 በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ በተፈጠረው ክስተት ነው።
በጨዋታው ተጨማሪ ሰዓት አሰልጣኙ ዳኛን በመሳደባቸው ቀይ ካርድ ተሰጥቷቸዋል። ቀይ ካርድ ከተሰጣቸው በኋላምሜዳውን ለቀው ባለመውጣታቸው 6 ጨዋታዎች ተቀጥተዋል። በተጨማሪም አራተኛ ዳኛን በመጋፈጥ ጨዋታውለሦስት ደቂቃ ያህል እንዲቋረጥ በማድረጋቸው 4 ተጨማሪ ጨዋታዎች ተቀጥተዋል። በዚሁ ጨዋታ የወላይታ ድቻደጋፊዎች በረዳት ዳኛ ላይ ድንጋይ በመወርወራቸው ክለቡ 50,000 ብር ተቀጥቷል።
አሰልጣኝ መሳይ በተረጋጋ ባህሪያቸው የሚታወቁ በመሆናቸው ድርጊቱ በስፖርቱ ማኅበረሰብ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያሆኗል።
ኢትዮጵያ ቡና በነገሌ አርሲ 3 ለ 0 ተሸነፈ፤ የደጋፊዎቹ ምላሽ ግን አድናቆት አስገኘ
ኢትዮጵያ ቡና ማክሰኞ ጥቅምት 11 በአዲስ አበባ ስታዲየም በነገሌ አርሲ 3 ለ 0 ተሸንፏል። ለነገሌ አርሲ ገብረመስቀልዱባለ፣ ዳዊት ተፈራ እና ጋናዊው ኮሊንስ ኮፊ ግቦቹን አስቆጥረዋል። የቡናው ተከላካይ ድልአዲስ ገብሬ በቀይ ካርድከሜዳ ወጥቷል። ነገሌ አርሲ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን በማስመዝገብ ከ11ኛ ወደ 2ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል። ቡናደግሞ ወደ 10ኛ ደረጃ ወርዷል።
የቡና ደጋፊዎች ሽንፈቱን በፀጋ ተቀብለው ለተጫዋቾቻቸው ድጋፋቸውን ማሳየታቸው የሳምንቱ ውብ ስፖርታዊጨዋነት ተደርጎ ተወስዷል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ3ኛ ሳምንት ሸገር ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል አስመዝግቧል።በዚሁ ጨዋታ የክለቡ ተጫዋች አቤል ሀብታሙ ሰብዓዊነትንና ፍትሐዊነትን ያስቀደመ ተግባር ፈጽሟል። ድርጊቱምከስፖርት ቤተሰቡ አድናቆትን አትርፎለታል።
ከሦስት ሳምንታት በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ን የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ7 ነጥብ ይመራል።የባህር ዳር ከተማው አንተነህ ተፈራ ደግሞ በ3 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ይመራል።
የ4ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 14፦ ሀዲያ ሆሳዕና ከ ፋሲል ከነማ፣ ከቀኑ 9:00 ሰዓት፣ አቢዮ ኤርሳሞስታዲየም (ሆሳዕና)
በቀጣዮቹ ቀናት የሚደረጉ ጨዋታዎች
- ሀላባ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ
- ነገሌ አርሲ ከ አዳማ ከተማ
- ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ኢትዮጵያ ቡና
- ሸገር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ ባህር ዳር ከተማ እና ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማየተራዘሙት በአህጉራዊ ውድድሮች ምክንያት የተራዘሙ ጨዋታዎች ናቸው ።
What's Your Reaction?