በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመው አስደንጋጭ የሬሳ ክፍሎች ዝርፊያና የ53 ሚሊዮን ዶላር ካሳ!

ለህክምና ምርምርና ለተማሪዎች ትምህርት ይሆን ዘንድ አካላቸውን ለታላቁ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በበጎ ፈቃደኝነት የለገሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች፣ ከሞት በኋላ የገጠማቸው እጣ ፈንታ የመላው ዓለምን ሕዝብ ያስቆጣና ያስደነገጠ ሆኗል።

Aug 20, 2026 - 17:21
 0  3
በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመው አስደንጋጭ የሬሳ ክፍሎች ዝርፊያና የ53 ሚሊዮን ዶላር ካሳ!



ለህክምና ምርምርና ለተማሪዎች ትምህርት ይሆን ዘንድ አካላቸውን ለታላቁ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በበጎ ፈቃደኝነት የለገሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች፣ ከሞት በኋላ የገጠማቸው እጣ ፈንታ የመላው ዓለምን ሕዝብ ያስቆጣና ያስደነገጠ ሆኗል።

ለአመታት ሲያገለግል የነበረ የዩኒቨርሲቲው አስክሬን ክፍል ኃላፊ፣ የለጋሾችን አስክሬን በድብቅ በመቁረጥ የሰው ልጅ የሰውነት ክፍሎችን በጥቁር ገበያ ሲሸጥ መቆየቱ ይፋ ሆኗል።

አስደንግጭ የዝርፊያ መረብሁኔታ ለሰላሳ ዓመታት ያህል በሃርቫርድ ህክምና ትምህርት ቤት የአስክሬን ክፍል ስራ አስኪያጅ የነበረው ሴድሪክ ሎጅ የተባለ ግለሰብ፣ ከ2018 እስከ 2022 ባሉት ዓመታት ውስጥ የተለገሱ አስክሬኖችን በድብቅ በመበጣጠስ የአንጎል፣ የቆዳ፣ የፊት፣ የእጅና የውስጥ አካላትን ሲዘርፍ ቆይቷል።

ሴድሪክ የተዘረፉትን የሰውነት ክፍሎች ወደ ቤቱ በመውሰድ ከባለቤቱ ጋር በመሆን በተለያዩ የአሜሪካ ክፍለ ሀገራት ለሚገኙ ገዢዎች በፖስታና በካርጎ ይልኩ ነበር። የተወሰኑት ገዢዎች ደግሞ ክፍሎቹን መልሰው ለሌሎች ሰዎች በውድ ዋጋ ይሸጡት እንደነበር ተደርሶበታል።

ሴድሪክ ሎጅ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የስምንት ዓመት የእስራት ፍርድ የተጣለበት ሲሆን፣ ባለቤቱና ሌሎች በጥቁር ገበያ ትስስሩ ላይ የተሳተፉ አጋሮቹም የእስር ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

የ53 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ስምምነት የሟች ቤተሰቦች ዩኒቨርሲቲው የቅርብ ዘመዶቻቸውን አካል በአግባቡ ባለመጠበቁና ቁጥጥር ባለማድረጉ ከፍተኛ የነፍስና የሕሊና እሰከቶች ደርሶብናል በማለት በጋራ ክስ መስርተው ነበር። ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየ ሲሆን፣ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ክሱን ከፍርድ ቤት ውጭ ለመጨረስ የ53 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ ለመፈጸም ተስማምቷል።

ከገንዘብ ካሳው በተጨማሪ የሃርቫርድ ህክምና ትምህርት ቤት አመራሮች ለተጎጂ ቤተሰቦች በቀጥታ በቪዲዮ መድረክ ይቅርታ ለመጠየቅና ድርጊቱ "የሞራል ውድቀት" እንደነበር ለመቀበል ተስማምተዋል። በተጨማሪም ለለጋሾቹ መታሰቢያ የሚሆን ዓመታዊ የስኮላርሺፕ ፈንድ እንደሚያቋቁሙና የአስክሬን ክፍሉን ጥበቃ ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠናክሩ አስታውቀዋል

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow