የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2029 በናይሮቢ 2031 በጀርመኗ ሙኒክ ይዘጋጃል

የዓለም አትሌቲክስ አዲሱ አቅጣጫ የዓለም አትሌቲክስ ውድድሮቹን በ3 ተከታታይ ጊዜያት በ3 የተለያየ አህጉራት እስያ ቤጂንግ 2027፣ አፍሪካ ናይሮቢ 2029  እና አውሮፓ ሙኒክ 2031 ለማካሄድ የያዘውን ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂ ያሳያል።

Sep 15, 2026 - 14:11
 0  1
የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2029 በናይሮቢ 2031 በጀርመኗ ሙኒክ ይዘጋጃል

ናይሮቢ የ2029 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ለማስተናገድ ተመረጠች።

የዓለም አትሌቲክስ ምክር ቤት በቡዳፔስት ባካሄደው 242ኛ ጉባኤ፣ የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የ2029 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዘጋጅ ከተማ ሆና መመረጧን አስታወቀ።

ይህ ውድድር በዓለም አትሌቲክስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ አህጉር የሚካሄድ ሲሆን፣ ለቀጣናው የስፖርት እና የኢኮኖሚ እድገት ትልቅ ማይልስቶን ተደርጎ ተወስዷል።

ውሳኔው ታሪካዊ ውሳኔ ነው ምክንያቱም የአለን አትሌቲክስ መድረክን የሚያደምቁት ኬንያውያን አትሌቶችን የምታፈልቀው ናይሮቢ እንደ ለንደን ካሉ ከተሞችን በመብለጥ ነው የ2029 ውድድርን የማስተናገድ መብት ያገኘችው።

ዝግጅቱ የሚካሄድበት ታዋቂው የካሳራኒ ስታዲየም ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ (AFCON) እና ለ2029 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፍተኛ የእድሳት እና የማስፋፊያ ሥራ እየተሰራበት ይገኛል። ከ2029 የናይሮቢ ውድድር በኋላ፣ የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ደግሞ በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ ይካሄዳል።


#

የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለጀርመኗ ሙኒክ ከተማ ተሰጠ

የዓለም አትሌቲክስ አዲሱ አቅጣጫ የዓለም አትሌቲክስ ውድድሮቹን በ3 ተከታታይ ጊዜያት በ3 የተለያየ አህጉራት እስያ ቤጂንግ 2027፣ አፍሪካ ናይሮቢ 2029  እና አውሮፓ ሙኒክ 2031 ለማካሄድ የያዘውን ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂ ያሳያል።

የዓለም አትሌቲክስ ምክር ቤት በቡዳፔስት ባካሄደው ስብሰባ፣ የ2029ኙን ውድድር ለናይሮቢ ከሰጠ በኋላ፣ የሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ የሚካሄደውን የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ ለማካሄድ ወስኗል።ውድድሩ በታዋቂው የሙኒክ ኦሊምፒክ ስታዲየም (Olympiastadion) የሚካሄድ ይሆናል።

ጀርመን እ.ኤ.አ. በ2009 በበርሊን ከተማ ካስተናገደች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ውድድርን ታስተናግዳለች።

ውድድሩ የአካባቢ ጥበቃና ዘላቂነትን መመሪያ ያደረገ እንዲሁም ከባህልና ጥበብ ፌስቲቫል ጋር የተቀናጀ ይሆናል።ከ2027 ቤጂንግ ቀጥሎ፣ የናይሮቢ 2029 እና የሙኒክ 2031 ውድድሮች በሙሉ በሴፕቴምበር መስከረም  ወር ይካሄዳሉ።

የጀርመኗ ሙኒክ ከተማ የ2031 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን እንድታዘጋጅ ተመርጣለች። ይህም አገሪቱ ከ2009 የበርሊን ውድድር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ትልቁን የዓለም አትሌቲክስ መድረክ የምታስተናግድበት ይሆናል። ውድድሩ በታዋቂው የሙኒክ ኦሊምፒክ ስታዲየም (Olympiapark) የሚካሄድ ሲሆን፣ ከስፖርታዊ ፉክክሩ ባሻገር የኪነ-ጥበብ እና የባህል ፌስቲቫልን ያካተተ ልዩ አህጉራዊ ዝግጅት እንደሚሆን ታቅዷል።


#LomiiNews #Nairobi2029 #WorldAthletics #EastAfrica #SportsNews #Ethiopia #Kenya #Munich2031 #WorldAthletics #SportsNews #Germany

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow