ከፔንታገን የ90 ቀናት ዕቅድ በስተጀርባ ያለው እውነት

Nov 4, 2026 - 12:05
Nov 4, 2026 - 12:07
 0  6
ከፔንታገን የ90 ቀናት ዕቅድ በስተጀርባ ያለው እውነት

በአሁኑ ወቅት እንደ ብሪታንያ፣ ጃፓን እና በርካታ የአውሮፓ አገራት መንግሥታት ዜጎቻቸው በድንገተኛ አደጋ ጊዜ ቢያንስ ለ72 ሰዓታት የሚበቃ ምግብ፣ ውሃ፣ የመጀመሪያ እርዳታ መሣሪያዎችና የኃይል አማራጮችን በቤታቸው እንዲያዘጋጁ እያሳሰቡ ይገኛሉ።

ይህ ጥሪ በብዙሃኑ ዘንድ "የሦስተኛው ዓለም ጦርነት ዋዜማ?" ወይም አስከፊ የተፈጥሮ አደጋ ስጋት የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳ ሲሆን ከጀርባው ያለው እውነት ግን የዓለም ፍጻሜን ሳይሆን የዘመናዊ አገራትን የተቀናጀ የሲቪል መከላከል ባህል (Civil Defense Culture) የሚያሳይ ነው ተብሏል። 

በታሪክ በተለይም በቅርብ ጊዜው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጀመሪያ ሰሞን ሕዝቡ መደናገጥ ውስጥ በመግባት ያደረገው የቁሳቁስ ሽሚያና የገበያ መታወክ መንግሥታትን ትልቅ ትምህርት የሰጠ በመሆኑ አሁን የሚወጡት መመሪያዎች ያንን የመደናገጥ ታሪክ ለመከላከልና ማኅበረሰብን አስቀድሞ በስነ-ልቦናም ሆነ በቁሳቁስ ለማዘጋጀት የታቀዱ ነባር አሠራሮች ናቸው። 

በተመሳሳይ ሁኔታ የአሜሪካው ፔንታገንም የጦር ሰፈሮቹ ያለ ውጭ እርዳታ ለ90 ቀናት እንዲቆዩ ማቀዱ የብሔራዊ ደኅንነት ተቋማትን የመቋቋም አቅም (Resilient) አካል ነው።

ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያን ይመለከታል ወይ? ለሚለው ጥያቄ ምላሹ አዎ፣ በተዘዋዋሪም በቀጥታም ይመለከታታል የሚል ነው። 

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈጠሩ የሳይበር ጥቃቶች፣ የጂኦፖለቲካ ውጥረቶችና የአየር ንብረት ለውጦች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሀገራትን በዋጋ ንረት፣ በስንዴና ነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል እንዲሁም በዓለም አቀፍ ድጋፎች መዘግየት በኩል ተጽዕኖ ማሳረፋቸው የማይቀር ነው።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow