አሜሪካ እና ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ የአጸፋ ጥቃት ተለዋወጡ
የአሜሪካ የጦር ሄሊኮፕተር በኢራን ድሮን መመታቷን ተከትሎ፣ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ በሚገነቱ የኢራን የአየር መከላከያ እና የራዳር ጣቢያዎች ላይ የአጸፋ ጥቃት ፈጽማለች።
የአሜሪካ የጦር ሄሊኮፕተር በኢራን ድሮን መመታቷን ተከትሎ፣ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ በሚገነቱ የኢራን የአየር መከላከያ እና የራዳር ጣቢያዎች ላይ የአጸፋ ጥቃት ፈጽማለች።
የአሜሪካ ወታደራዊ ማዕከላዊ ዕዝ እንዳስታወቀው፣ ጥቃቱ የተሰነዘረው በሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ በሚገኙ የኢራን የአየር መከላከያ፣ የምድር መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች እና ራዳሮች ላይ ነው። ዋሽንግተን ድርጊቱ በባሕረ ሰላጤው ላይ ለተመታችው የጦር ሄሊኮፕተር የተመጣጠነ ምላሽ መሆኑን ገልጻለች።
በሌላ በኩል ኢራን ለሄሊኮፕተሯ መውደቅ ኃላፊነቱን ባትወስድም፣ ለአሜሪካው ድብደባ ምላሽ ለመስጠት በባህሬን እና ዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ የሮኬት ጥቃት መሰንዘሯን አስታውቃለች። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሁለቱ ሀገራት በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ውስጥ ባለ 21 ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ይፋ አድርጓል።
ለተፈጠረው ውጥረት ምላሽ የሰጡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ለጥቃቱ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም ዋሽንግተን እና ቴህራን የቀጣናውን ጦርነት ለማቆም በድርድር ላይ በመሆናቸው፣ ሁለቱም ወገኖች በአስቸኳይ ተኩስ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
በተቃራኒው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ አሜሪካ ጥቃት መፈጸሟን እንድታቆም አስጠንቅቀዋል። ሚኒስትሩ አጽንዖት በመስጠት እንደተናገሩት፣ የውጭ ኃይሎች ደኅንነታቸው እንዲጠበቅ ከፈለጉ ቀጣናውን በአስቸኳይ ለቀው መውጣት ይኖርባቸዋል።
ቢቢሲ እንደዘገበው በሁለቱ ኃይሎች መካከል ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ እና የቃላት ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
What's Your Reaction?