የሕብረት ሥራ ማህበራትን ሕይወት የሚቀይረው አዲስ አዋጅ ጸደቀ!

የሕብረት ሥራ ማህበራትን ሕይወት የሚቀይረው አዲስ አዋጅ ጸደቀ! ባለሀብቶችን በርግጥ የሀብት ባለቤት የሚያደርገውእና  ሴቶችን ወደ አመራርነት የሚያወጣው ታሪካዊው አዋጅ ነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው 21ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የሕብረት ሥራ ማህበራትን አሠራር ከነበረበት ልምዳዊ አሠራር አውጥቶ ወደ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ የሚያሸጋግር አዲስ አዋጅ አጽድቋል።

May 14, 2026 - 19:46
 0  1
የሕብረት ሥራ ማህበራትን ሕይወት የሚቀይረው አዲስ አዋጅ ጸደቀ!

የሕብረት ሥራ ማህበራትን ሕይወት የሚቀይረው አዲ አዋጅ ጸደቀ! ባለሀብቶችን በርግጥ የሀብት ባለቤት የሚያደርገውእና  ሴቶችን ወደ አመራርነት የሚያወጣው ታሪካዊው አዋጅ ነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው 21 መደበኛ ስብሰባው፣ የሕብረት ሥራ ማህበራትን አሠራር ከነበረበት ልምዳዊ አሠራር አውጥቶ ወደ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ የሚያሸጋግር አዲስ አዋጅ አጽድቋል። ይህ አዋጅ የማህበራቱን የቆየ ችግር የሚፈታና አባላቱን የሀብት ባለቤት የሚያደርግ እንደሆነ ተነግሮለታል።

 አዲሱ አዋጅ ማህበራቱ ካላቸው ድርሻ እስከ 40 በመቶ የሚሆነውን ለባለሀብቶች መሸጥ የሚችሉበትን ወርቃማ ዕድል ፈጥሯል። ይህም ማህበራቱ መሬትና መጋዘን ሲያቀርቡ፣ ባለሀብቱ ደግሞ ካፒታልና ቴክኖሎጂ ይዞ በመግባት በጋራ እንዲበለጽጉ መንገድ ይከፍታል።

ከዚህ በተጨማሪ በአመራርነት ደረጃ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ አሰራር ተዘርግቷል፦50 በመቶ የአመራርነት ድርሻ ለሴቶች!10 በመቶ ለወጣቶች! እና 10 በመቶ ለአካል ጉዳተኞች የሚያደርግ አሰራር የዘረጋ ሲሆን ይህ ድንጋጌ ማህበራቱ የሁሉንም ድምጽ የሚሰሙና ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ተብሎዋልማህበራቱ በተበታተነ መልኩ መስራታቸው ቀርቶ እንዲቀናጁ በመደረጉ፣ የአሠራር ድግግሞሽና አላስፈላጊ ብክነት ይቆማል። በምትኩ በሰለጠነ የሰው ኃይልና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር ይነግሳል።

 የሎሚ ዜና ትንታኔ፦ይህ አዋጅ በተለይ በግብርናው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የሕብረት ሥራ ማህበራት ካፒታል እንዲያሳድጉና የውጭ ገበያን በብቃት እንዲቀላቀሉ ትልቅ በር ይከፍታል።

ሎሚ ዜናየለውጥ ድምጾችን እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያደርሳል!

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow