ኔታንያሁ በምስጢር ኤምሬትስን ጎብኝተዋል መባሉ ውዝግብ አስነሳ

ታንያሁ በምስጢር ኤምሬትስን ጎብኝተዋል መባሉ ውዝግብ አስነሳ በእስራኤል እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አዲስ አነጋጋሪ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ይመስላል።

May 14, 2026 - 19:30
 0  1
ኔታንያሁ በምስጢር ኤምሬትስን ጎብኝተዋል መባሉ ውዝግብ አስነሳ

በእስራኤል እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አዲስ አነጋጋሪ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ይመስላል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ቢሮ ኔታንያሁ በኤምሬትስ አል አይን ከተማ ምስጢራዊ ጉብኝት ማድረጋቸውንና ከፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መምከራቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መረጃውን በይፋ አስተባብላለች።

የኤምሬትስ መንግስት የዜና ወኪል ባወጣው መግለጫ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት በአብርሃም ስምምነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚመራና ግልጽነት ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ማንኛውም ዓይነት "ምስጢራዊ ወይም ድብቅ" የተባለ ግንኙነት እንደሌለና ስለ ጉብኝቱ የሚናፈሰው መረጃም መሠረተ ቢስ መሆኑን አስታውቋል።

​ይህ በእንዲሁ እንዳለ፣ የኔታንያሁ ቢሮ ጉብኝቱን "ታሪካዊ" በማለት የገለጸው ኢራን በኤምሬትስ ላይ ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች በሚል ስጋት በነበረበት ወቅት መከናወኑን ጠቁሟል። በተመሳሳይ ሁኔታ በእስራኤል የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ እስራኤል የኢራንን ጥቃት ለመመከት የአይረን ዶም የአየር መከላከያ መሳሪያዎቿንና የቴክኒክ ባለሙያዎቿን በኤምሬትስ ምድር ማሰማራቷን መግለጻቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የጸጥታ ትብብር ከቃላት ባለፈ ወደ ተግባር እየተሸጋገረ መሆኑን አመላካች ሆኗል።

አምባሳደሩ በቴል አቪቭ በነበራቸው ቆይታ የባህረ ሰላጤው ሀገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት እያጠናከሩ መምጣታቸውን አድንቀዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow