የተሽከርካሪ ሰሌዳዎችን የማዘመን ሂደትና በአሽከርካሬዎች ላይ የተጋረጠው የኢኮኖሚ ጫና
የኢፌዴሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወይም የክልል ትራንስፖርት ቢሮ አዲስ ያዘጋጀውን ዘመናዊ የተሽከርካሪዎች ሰሌዳ በሂደት ወደ ሥራ ማስገባት መጀመሩ ይታወቃል።
የኢፌዴሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወይም የክልል ትራንስፖርት ቢሮ አዲስ ያዘጋጀውን ዘመናዊ የተሽከርካሪዎች ሰሌዳ በሂደት ወደ ሥራ ማስገባት መጀመሩ ይታወቃል።
ይህ አዲስ የሰሌዳ ሥርዓት በተሽከርካሪዎች ደህንነትና በትራፊክ ቁጥጥር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ቢነገርም፤ አሁን ካለው የኑሮ ውድነት እና የኢኮኖሚ ጫና አንጻር አተገባበሩ አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጉዳይ በማኅበረሰቡና በዘርፉ ባለሙያዎች ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ዝርዝር ዘገባውን ይዘን ቀርበናል።
መንግሥት ወደ ሥራ ያስገባቸው አዲሶቹ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች የረቀቁ የደህንነት ምልክቶችን (Watermarks) እና የዲጂታል መረጃ ትስስር ቴክኖሎጂዎችን ያካተቱ ናቸው። የአተገባበር ሂደቱም ነባሮቹን ታርጋዎች በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሳይሆን፤ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ሲመዘገቡ፣ የስም ዝውውር ሲደረግ እና ዓመታዊ የቦሎ እድሳት በሚከናወንበት ወቅት ደረጃ በደረጃ የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።
ይህ አሰራር በሀገሪቱ እየታየ ያለውን የተሽከርካሪ ስርቆት፣ የሐሰተኛ ታርጋ ማተም ወንጀልን እና የትራፊክ ደንብ መጣስን በዘመናዊ መሣሪያዎች ለመቆጣጠር ፍፁም አስፈላጊ መሆኑን ባለሙያዎቹ ያሰምሩበታል።
ይሁን እንጂ የአዲሱ ሰሌዳ ሽያጭና ተያያዥ ክፍያዎች ከወቅቱ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከምና ከዋጋ ንረት ጋር ተዳምሮ በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ተጨማሪ የወጪ ጫና እያሳደረ ነው በሚል የሚተቹም አሉ።
በርካታ የአሽከርካሪዎችና የትራንስፖርት ማኅበራት አሁን ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ የሰሌዳ ሌላ ወጪ መጨመር በተለይም በሕዝብና በጭነት ትራንስፖርት ላይ የሚሰማሩ ባለቤቶችን ክፉኛ እንደሚፈታተን ይገልጻል።
ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች ሀሳባቸውን እንዲህ ሲሉ ይጀምራሉ። "የታርጋው ዘመናዊ መሆን እና ደህንነቱ መጠበቁ ጥሩ ነው። ነገር ግን አሁን ባለንበት ሁኔታ የመለዋወጫ ዕቃዎች ዋጋ ሰማይ የነካበት፣ የነዳጅ ዋጋ የጨመረበት ወቅት በመሆኑ፣ ለታርጋ የሚወጣው ተጨማሪ ክፍያ ሌላ ጫና ነው የሚሆንብን።" ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስተያየት ደግሞ "ቴክኖሎጂው ለሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ደህንነትና ለከተማ ውበት ፍፁም አስፈላጊ ነው። ነገር ግን አፈጻጸሙ የሕዝቡን የኢኮኖሚ አቅም ባገናዘበ መልኩ ምናልባትም ክፍያዎቹን በረጅም ጊዜ የጊዜ ሰሌዳ መክፈል በሚቻልበት አግባብ ቢሆን የተሻለ ተቀባይነት ያገኝ ነበር።"ብለዋል።
በአጠቃላይ አዲሱ የሰሌዳ አተገባበር በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመንና ወንጀልን ለመከላከል ያለው አስፈላጊነት አጠራጣሪ ባይሆንም፤ በወቅታዊው የገንዘብ ውድነት ወቅት መተግበሩ ግን በባለቤቶች ላይ የኢኮኖሚ ፈተና መደቀኑ አልቀረም። ይህንን ክፍተት ለመሙላት መንግሥት የአገልግሎት ክፍያዎችን ማቅለልና አሰራሩን ይበልጥ ተደራሽ ማድረግ እንዳለበት እንጠቁማለን።
What's Your Reaction?