የዋሽንግተን እና የሞስኮ ዲፕሎማሲ፡

ሰላም ንግግር በአንድ በኩል፣ ሚሳኤል በሌላ በኩል  ሩሲያ  በዚህ ኪየቭን በሚሳየል  እመታች፤ በዚያ ደግሞ ፑቲን አሜሪካዊ እስረኛ ይፈታሉ ። ይህ ጦርነት የስንዴና የማዳበሪያ ዋጋን ይነካል  ስለዚህ ለእኛም ይመለከተናል! ሎሚ ኒውስ 

Oct 23, 2026 - 10:55
 0  3
የዋሽንግተን እና የሞስኮ ዲፕሎማሲ፡

በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም አዳዲስ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች እና የሰላም ንግግሮችዳግም በተጀመሩበት በዚህ ወቅት፣ በምስራቅ አውሮፓ የቀጠለው ውጥረት አዳዲስ ሁነቶችን እያሳየ ይገኛል። ይህሁነት የሚያሳየው በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ትልልቅ ሀገራት (አሜሪካ እና ሩሲያ) የራሳቸውን የዲፕሎማሲግንኙነት ለማቃናት በሚያደርጉት ጥረት መካከል፣ በዩክሬን አሁንም ጥቃቶች እና የጦርነት ቀጣናዎች አለመረጋጋትእንደቀጠሉ መሆናቸውን ነው። የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ እና በጂኦ-ፖለቲካዊሁኔታዎች ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው።

 የሰላም ንግግር ጥረቶች በልዩ መልዕክተኞች በኩል እየተደረጉ ቢሆንም፣ የሩሲያ ሚሳይሎች እና ድሮኖች የዩክሬን ዋናከተማ ኪየቭን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽመዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአራት ዓመታት ገደማ በሩሲያ እስር ቤት ታስረው የቆዩትን አሜሪካዊውን ስቲቨንሁባርድን ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

ይህ እስረኛ ልውውጥ ያለ ምንም የፋ ያልወጣ ቅድመሁኔታ  መፈታቱ በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለው የዲፕሎማሲግንኙነት መሻሻል ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል። የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ከፑቲን ጋር በሴንትፒተርስበርግ ያደረጉት ውይይት ለሶስትዮሽ የሰላም ንግግሮች መንገድ እየከፈተ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

"ሰላም እያወሩ ሚሳኤል ይተኩሳሉ! ሩሲያና ዩክሬን የሰላም ንግግር በድጋሚ ጀምረዋል — በዚያው ሰሞን ኪየቭ በሚሳኤል ተመታች። ፑቲን ደግሞ አንድ አሜሪካዊ ፈቱ። ይህ ጦርነት የስንዴና የማዳበሪያ ዋጋን ይነካል — ስለዚህ ለእኛም ይመለከተናል! ሎሚ ኒውስ

 #LomiiNews #ሩሲያ #ዩክሬን #ሰላም

 

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow