በመኪና ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች፦ ዘመናዊ መኪናዎች የእርስዎን የግል መረጃ እየሰረቁ ይሸጣሉ

መኪናዎ ስለ እርስዎ የሚሰበስበው አስደንጋጭ መረጃ እና የኢንሹራንስ ዋጋ መጨመር! ዘመናዊ መኪናዎች ስለ እርስዎ የሰውነት ክብደት፣ የፊት ገጽታ እና ስለሚሄዱበት ቦታ አስገራሚ መረጃዎችን እየሰበሰቡ እንደሆነ ያውቃሉ?በመኪና ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች፦ ዘመናዊ መኪናዎች የእርስዎን የግል መረጃ እየሰረቁ ይሸጣሉ  

May 28, 2026 - 15:35
May 28, 2026 - 19:29
 0  1
በመኪና ላይ ያሉ ኮምፒውተሮች፦ ዘመናዊ መኪናዎች የእርስዎን የግል መረጃ እየሰረቁ ይሸጣሉ

በሎሚ ኒውስ የቴክኖሎጂ እና የመኪና ዘርፍ ዴስክ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20/2018 .

የመኪና ቁልፍ መያዝ ቀደም ባሉት ጊዜያት የነፃነት ምልክት ነበር፤ ከወላጆች ቁጥጥር ወጥቶ የራስን ውሳኔ በራስ የመወሰኛ መንገድ። ነገር ግን ጊዜያት ተቀይረዋል። ዛሬ ላይ ዘመናዊ መኪናዎችበጎማ ላይ የቆሙ ኮምፒውተሮችሆነዋል፤ ግዙፍ ኮርፖሬሽኖችም ስለ እርስዎ የግል ሕይወት ጥቃቅን ምስጢሮችን በመሰብሰብ ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ።

መኪና መንዳት አሁንም ቢሆን የብቸኝነት እና የነፃነት ጊዜ መስሎ የሚታይዎት ከሆነ፣ ነገሩን እንደገና ሊያስቡበት ይገባል። እንዲያውም ሁኔታው ወደፊት ይበልጥ የከፋ እንደሚሆን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የመኪና አምራቾችን የግል ምስጢራቸውን አጠባበቅ መመሪያዎች በጥልቀት ካነበብናቸው፣ የሚሰበስቡትን አስገራሚ የመረጃ መጠን ራሳቸው በግልጽ ያመኑበት ሆኖ እናገኘዋለን። መኪናዎ የሚከተሉትን መረጃዎች በየቀኑ ይሰበስባል፦

·       የሚሄዱበትን ትክክለኛ ቦታ (Location) አብሮዎት ማን እንዳለ እና በራዲዮ ምን እየሰሙ እንደሆነ።

·       የደህንነት ቀበቶ ማሰርዎን፣ በፍጥነት መንዳትዎን ወይም ብሬክ በኃይል መርገጥዎን።

·       ከእነዚህም ባለፈ የእርስዎን የሰውነት ክብደት፣ ዕድሜ፣ ዘር እና የፊት ገጽታ መግለጫዎችን (Facial Expressions) ጭምር።

አንዳንድ መኪናዎች ወደ አሽከርካሪው ወንበር የተቀሰሩ የውስጥ ካሜራዎች አሏቸው። አብዛኛዎቹ ዘመናዊ መኪናዎች ደግሞ የኢንተርኔት ግንኙነት ስላላቸው፣ እርስዎ በደስታ መኪናዎን እየነዱ ባሉበት ወቅት እነዚህን መረጃዎች በቀጥታ ወደ አምራቾቹ ዛሉ።

ይህ የግል ምስጢር መጣስ መብት ብቻ ሳይሆን፣ በቀጥታ በኪስዎ ላይ ጉዳት የሚያደርስ የገንዘብ ችግርም ጭምር ነው። በተለይ በውጭ የምትኖሩ የእነዚህ መኪናዎች መረጃ ዋነኛ ገዢዎች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ናቸው። ኩባንያዎቹ የእርስዎን የአነዳድ ዘይቤ በመገምገም የኢንሹራንስ ክፍያ ዋጋዎን (Insurance Premium) ለመጨመር ይጠቀሙበታል።

አብዛኛዎቹ የመኪና ኩባንያዎች መረጃዎን ለሌሎች እንደሚሸጡ ቢያምኑም፣ በትክክል ማን እንደሚገዛቸው ግን ለመናገር አይገደዱም። በጣም የሚያሳዝነው ግን፣ አብዛኛዎቹ የመኪና ባለቤቶች ይህ ሁሉ ነገር እየተከናወነ መሆኑን በፍጹም አለማወቃቸው ነው።

ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፣ መኪናዎ ስለ እርስዎ የሚያውቀውን መረጃ መጠን ለመገደብ አንዳንድ ቀላል እርምጃዎችን መውሰድ ቢቻልም  ዋናው መፍትሔ ተጠቃሚዎች ስለ ጉዳዩ ንቁ መሆን መቻላቸው ነው።

የሎሚ ኒውስ ምክር፦ መኪናዎ ስለ እርስዎ የሚያውቀውን መረጃ ለመቀነስ በመኪናው ሲስተም ውስጥ ያሉትን 'Privacy Settings' እና መረጃ የማጋራት (Data Sharing) አማራጮችን መዝጋትዎን ያረጋግጡ!

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow