የኤ.ኤ.ዩ የቴክኖሎጂ ኮሌጅ እና ሀገራዊ የልማት ተሳትፎ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ እና ቢዩልት ኢንቫይሮመንት ኮሌጅ ከመማር ማስተማር ተግባሩ ባሻገር ሀገርንና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ግዙፍ የልማትና የምርምር ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ እንደሚገኝ ተዘግቧል። 

May 21, 2026 - 13:47
 0  3
የኤ.ኤ.ዩ የቴክኖሎጂ ኮሌጅ እና ሀገራዊ የልማት ተሳትፎ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ እና ቢዩልት ኢንቫይሮመንት ኮሌጅ ከመማር ማስተማር ተግባሩ ባሻገር ሀገርንና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ግዙፍ የልማትና የምርምር ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ እንደሚገኝ ተዘግቧል። 

የኮሌጁ የምርምር እና ተሳትፎ ምክትል ኤክስኪዩቲቭ ዲን ዶ/ር ጌታሰው አሻግሬ  እንደገለጹት፤ ተቋሙ ለሀገር ልማትና ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽዖ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን፣ ለዚህም በምሳሌነት ሊጠቀሱ በሚችሉት የታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ እንዲሁም የአዳማ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታዎች ላይ የኮሌጁ ምሁራን ከፍተኛ የሙያ ተሳትፎ አድርገዋል።

 ኮሌጁ በእነዚህ ወሳኝ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ከመሳተፍ ባለፈ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች የማማከር አገልግሎት በመስጠትና ለተለያዩ የኢንዱስትሪ ተቋማት ሠራተኞች ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት በጥምረት እየሠራ እንደሚገኝ ያብራሩት ዶ/ር ጌታሰው፣ በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተከናወኑና እየተከናወኑ ባሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን ጠቁመዋል። 

አዳዲስ የልማት ሐሳቦችና ፕሮጀክቶች ይዘዋቸው የሚመጡት የራሳቸው ተግዳሮቶች መኖራቸውን ያነሱት ምክትል ኤክስኪዩቲቭ ዲኑ፣ ኮሌጁ በግንባታዎቹ ላይ ከመሳተፍ ባለፈ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች አስቀድመው እንዳይፈጠሩ ለመከላከልና በቀጣይ ፕሮጀክቶች ላይም በመምከር ማህበረሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ስልታዊ መንገድ ለማመቻቸት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow