በአሜሪካ እና በኢራን ስምምነት ምክንያት አውሮፓውያን ማዕቀብ ለማንሳት መዘጋጀታቸውን ገለጹ
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፤ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በኢራን ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ለማንሳት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፤ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በኢራን ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ለማንሳት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ። የአውሮፓ አገራት መሪዎች ማዕቀቡ የሚነሳው ቴህራን በኒውክሌር ፕሮግራሟ ላይ ግልጽ እና ሊረጋገጡ የሚችሉ እርምጃዎችን ስትወስድ መሆኑን ገልጸው፣ “ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማግኘት የለባትም” ብለዋል።
ለዚህም ዓላማ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ፣ ከአሜሪካ እና ከኢራን ጋር ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። መግለጫው በተጨማሪም የሆርሙዝ ባህር ያለገደብ እንዲከፈት እና የሊባኖስ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል፣ በኳታር አደራዳሪነት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በቀረበው የመግባቢያ ሰነድ ላይ ለመስማማት በቴህራን ከ14 እስከ 15 ሰአታት የፈጀ ረጅም ውይይት መደረጉን የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ ዛሬ ለመንግስት ሚዲያ አስታውቀዋል።
What's Your Reaction?