ከማዕቀብ ማንሳት እስከ እምነት ግንባታ፤ የኢራንና አሜሪካ አዲሱ የሰላም ረቂቅ
በኢራንና በአሜሪካ መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ውጥረት አቅጣጫ ሊያስቀይር የሚችል አዲስና አስገራሚ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ።
በኢራንና በአሜሪካ መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ውጥረት አቅጣጫ ሊያስቀይር የሚችል አዲስና አስገራሚ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ። የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው፣ ከሶስት ቀናት በፊት ቴህራን በፓኪስታን አምባሳደር አማካኝነት 14 ነጥቦችን ያካተተ የተሻሻለ የሰላም ረቂቅ ሰነድ ለዋሽንግተን ያስገባች ሲሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስም በበኩሏ የራሷን ማሻሻያና የውይይት ነጥቦች በዛሬው ዕለት በዚሁ በፓኪስታን በኩል ለቴህራን መልሳ ልካለች።
በአሁኑ ወቅት የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት የአሜሪካን ሰነድ በጥልቅ እየገመገሙት ቢሆንም እስካሁን ይፋዊ ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን፣ የፓኪስታን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሞህሲን ናቅቪም በቴህራን በመገኘት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉትን ሰፊ የሃሳብ ልዩነቶች ለማጥበብና ስምምነቱ እንዳይከሽፍ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
ምንም እንኳን አሜሪካ በድርድሩ ወቅት በኢራን ላይ የጣለችው ማዕቀብ ሊነሳ እንደሚችል ፍንጭ የሰጠች ቢሆንም፣ ኢራን ግን ሁሉንም ማዕቀቦች በአንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ለማንሳት የሚያስገድድ ስምምነት እንዲሆን በፅኑ እየወተወተች ሲሆን፣ ይህ የቴህራን 14 ነጥብ እቅድ በዋናነት የሚያተኩረውም ጦርነቱን ሙሉ በሙሉ ለማቆምና በአሜሪካ በኩል የእምነት ግንባታ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በሚሉ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ነው።
What's Your Reaction?