በኢትዮጵያ ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከአንበጣ መንጋ ተረፈ

በኢትዮጵያ ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከአንበጣ መንጋ ተረፈ የግብርና ሚኒስቴር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደውን የበረሃ አንበጣ የመከላከል ዘመቻ አስመልክቶ ባወጣው መረጃ፣ በከፍተኛ ጥረት 505 ሺህ ሄክታር መሬትን ከጥፋት መታደግ መቻሉን አስታውቋል።​በ11.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ሰፊ የክትትልና የዳሰሳ ስራ ተከናውኗል።

May 13, 2026 - 21:04
 0  3
በኢትዮጵያ ከ500 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከአንበጣ መንጋ ተረፈ

የግብርና ሚኒስቴር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደውን የበረሃ አንበጣ የመከላከል ዘመቻ አስመልክቶ ባወጣው መረጃ፣ በከፍተኛ ጥረት 505 ሺህ ሄክታር መሬትን ከጥፋት መታደግ መቻሉን አስታውቋል።​በ11.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ሰፊ የክትትልና የዳሰሳ ስራ ተከናውኗል።

​የተሸፈኑ አካባቢዎች ፕሮጀክቱ በ311 ወረዳዎች ውስጥ ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን፤ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ሐረሪ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ድሬዳዋን ያጠቃልላል።

​የበጀት ድጋፍ  ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም ባንክ ድጋፍ 123 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦለት እየተሰራ ይገኛል።

ምንም እንኳን አሁን ላይ አንበጣው የከፋ ስጋት ባይደቅንም፣ ሚኒስቴሩ የቅድመ መከላከል ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል። የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚው አቶ ይመር ዳውድ እንደገለጹት የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፦

​የአንበጣ ክስተትን ቀድሞ ማወቅ፣

​በምርታማነትና በግጦሽ ሳር ላይ

​ብሔራዊ የመቋቋም አቅምን ማጠናከር ነው።

​በአሁኑ ወቅት በዘመናዊ የኬሚካል ርጭት የታገዘ የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ ሲሆን፣ ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow