የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ስራ ሊከናወን እንደሚገባ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ዘንድ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሀብት ማሳወቅ እና ማስመዝገብ ስራ በሁሉም ኮሌጆች እየተከናወነ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አልማዝ ታፈሰ ገልጸዋል።

Jun 18, 2026 - 15:39
 0  2
የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ስራ ሊከናወን እንደሚገባ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ዘንድ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሀብት ማሳወቅ እና ማስመዝገብ ስራ በሁሉም ኮሌጆች እየተከናወነ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አልማዝ ታፈሰ ገልጸዋል። 

ሙስና የሚያስከትላቸውን ፈርጀ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ከባቢያዊ አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለመከላከል የሀብት ማሳወቅ እና ማስመዝገብ ስርዓት ጠንካራ ስትራቴጂ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፣ የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንም ይህንን አሰራር በአዋጅ ቁጥር 668/2002 መሰረት በመተግበር ላይ ይገኛል።

ይህ የሀብትና ጥቅም የማሳወቅ ሥርዓት ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ፣ ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን በማጋለጥ እና ለፍርድ ሂደት ማስረጃ በመሆን ሙስናን ለመግታት እንደሚያስችል የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ በአደጉ ሀገራት ሀብት ማሳወቅ ለግል ደህንነት የሚተገበር ስርዓት ቢሆንም በሀገራችን ግን ገና ግንዛቤ መፍጠር ላይ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመሆኑም በየኮሌጁ ያሉ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በኦንላይን አልያም በአካል በመምጣት የሀብት ማሳወቅ ምዝገባን በወቅቱ እንዲያከናኑ ጥሪ አቅርበዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow