የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሰሜን ኮሪያ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሰባት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜን ኮሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ፒዮንግያንግ ገብተዋል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሰባት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜን ኮሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ፒዮንግያንግ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ እና ባለቤታቸው ፔንግ ሊዩዋን አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና ባለቤታቸው ሪ ሶል ጁ ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በመቀጠልም በዋናው የከተማዋ አደባባይ በተካሄደው ደማቅ የስነ-ስርዓት ፕሮግራም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት፣ የክብር ዘቦች እና የሁለቱ ሀገራት ግዙፍ ባንዲራዎች እንዲሁም የመሪዎቹ ምስሎች በስፋት ታይተዋል።
ይህ ጉብኝት ምንም እንኳን ይፋዊ አጀንዳው በግልጽ ባይቀመጥም፥ ሁለቱ መሪዎች ከአሜሪካ ጋር ባለባቸው የተናጠል ፍጥጫ መሃል ታሪካዊ ጥምረታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ የፖለቲካ ምሁራን ይገምታሉ።
ቻይና በሰሜን ኮሪያ ላይ ያላትን ልዩ ተፅዕኖ ዳግም ለማረጋገጥ ስትሞክር፥ በምላሹም ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ድጋፎችን እንደምታደርግ ይጠበቃል።
ይህ በሁለቱ መሪዎች መካከል የሚደረገው የልዑካን ቡድን ስብሰባ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጣናዊ ፖለቲካ ላይ ትልቅ አንድምታ ይኖረዋል ተብሏል።
What's Your Reaction?