የአውሮፓ እና የፊፋ ፍልሚያ! ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ የስፖርት እና የኢኮኖሚ እድል ወይስ ስጋት?
የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (FA) እና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) በፊፋ ፕሬዚዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ላይ የከፈቱት ጠንካራ ተቃውሞ የዓለም እግር ኳስ ፖለቲካን እያናወጠው ይገኛል።
የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር (FA) እና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) በፊፋ ፕሬዚዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ላይ የከፈቱት ጠንካራ ተቃውሞ የዓለም እግር ኳስ ፖለቲካን እያናወጠው ይገኛል። ውዝግቡ በዋናነት የአውሮፓ ሀገራትን ጥቅም የሚነካ ቢሆንም ለአፍሪካ ሀገራት ግን ሙሉ በሙሉ የተለየ ትርጉም እና እድል ይዞ መጥቷል።
በፊፋ የአሰራር ደንብ መሰረት እያንዳንዱ አባል ሀገር እኩል 1 ድምፅ አለው። ይህ አሰራር 54 አባል ሀገራት ያሏትን አፍሪካ በፊፋ የውሳኔ ሰጪነት መድረክ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዲኖራት አድርጓታል።
በኢንፋንቲኖ አመራር ስር ለአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የሚሰጠው የልማት በጀት በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። ይህ ገንዘብ በታዳጊ ሀገራት ስታዲየሞችን ለመገንባት፣ የህፃናትና የሴቶች እግር ኳስን ለማስፋፋት እና የአሰልጣኞች ስልጠና ለመስጠት ውሳኝ መሰረት ሆኗል።
ከዚህ ሌላ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) እና አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት የኢንፋንቲኖን የፋይናንስ እና የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴዎች ስለሚደግፉ፣ ከአውሮፓ ተቃውሞ በተቃራኒው የኢንፋንቲኖ ዋና የስልጣን ደጋፊ ሆነው ቀጥለዋል።
ሌላው የፊፋ ፕሬዚዳንት በወሰዱት ውሳኔ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ከ 32 ወደ 48 እንዲያድግ ተደርጓል። ቀደም ሲል ለአፍሪካ ይሰጥ የነበረው የ 5 ሀገራት ኮታ አሁን ላይ ወደ 9 በቀጥታ + 1 በፕሌይ-ኦፍ (Play-off) ከፍ ብሏል።ይህ አሰራር ቀደም ሲል ወደ ዓለም ዋንጫ የማለፍ እድል ያልነበራቸው እንደ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ እና ማሊ ያሉ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የመሳተፍ እና ሀገራዊ እግር ኳሳቸውን የማሳደግ ትልቅ ተስፋ ፈጥሮላቸዋል።
በውዝግቡ ጀርባ ያለው የ $20 ቢሊዮን ዶላር የንግድ እቅድ የሳውዲ አረቢያ እና የባህረ-ሰላጤው ሀገራት የፋይናንስ እንቅስቃሴ አለበት ተብሎ ይወራል ። የአረብ ሀገራት በፊፋ እና በአፍሪካ እግር ኳስ ላይ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት መጨመር፣ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ አዳዲስ የስፖንሰርሺፕ ውሎችን እና የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት አዲስ በር ከመክፈቱም ባሻገር የአውሮፖ ሀገራት ብቻ ተቆጣጥረውት የነበረውን የስፖርት ማማ ወደሌሎች ሀግራትም ለማስፋፋት ምክንያት ሆነዋል ።
ታዲያ ስጋቱ ይህ ውዝግብ ተባብሶ አውሮፓውያን የዓለም ዋንጫን የሚቃወሙ እና ማእቅብ የሚያደርጉ ከሆነ፣ የዓለም ዋንጫ የነበረው የገበያ እና የቴሌቪዥን ስርጭት ዋጋ ሊወርድ ይችላል። ይህም በረጅም ጊዜ ለአፍሪካ ሀገራት የሚፈሰው የፊፋ የገንዘብ ድጎማ እንዳይቀንስ ስጋት ይፈጥራል።
የእንግሊዝ እና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበራት የኢንፋንቲኖን አካሄድ "የስፖርቱን ንግድ ለግል ሀብታሞች አሳልፎ መስጠት" ብለው ሲቃወሙት፤ ለአፍሪካ ሀገራት ግን የተሻለ የፋይናንስ ድጋፍ፣ የተስፋፋ የዓለም ዋንጫ ኮታ እና የመሰረተ ልማት እድገት ዋስትና ሆኖ በመታየቱ አህጉሪቱ ለጊዜውም ቢሆን ከኢንፋንቲኖ ጎን እንድትቆም አድርጓታል።
የአፍርካ እና የአለም ዋንጫ አቋም ለጊዜው ይህን ቢመስልም ውጤቱ ግን የሚታወቀ ውዝግቡ እየከረረ የሚሰጠው ማማለያ እየሰፋ ከመጣነው ። ይህንን አስደማሚ የግርኳስ ውዝግብ እና የሀይል ሽሚያ በቅርበት ለመከታተል ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት የሎሚ ስፖርትን ቤተሰብ ይሁኑ።
ምንጭ፦ Lomii Sport Desk / FIFA & CAF Strategic Reports
የስፖርት ዓለም አዳዲስ እና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት Lomii Sport መከታተልዎን ይቀጥሉ!
What's Your Reaction?