የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የቻይናው NCET በስማርት ትምህርት ልማት ላይ ተወያዩ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይናው ብሔራዊ የትምህርት ቴክኖሎጂ ማዕከል (NCET) ጋር በስማርት ትምህርት ልማት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይናው ብሔራዊ የትምህርት ቴክኖሎጂ ማዕከል (NCET) ጋር በስማርት ትምህርት ልማት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂዷል። በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው በዚህ ውይይት የስማርት ትምህርት መድረኮችን በጋራ ማሳደግ፣ የዲጂታል የትምህርት ግብዓቶችን መለዋወጥ፣ በትምህርት ዘርፍ የዳታ አጠቃቀምን ማጠናከር እና የመምህራንን የዲጂታል እውቀት ማሻሻል በሚቻልባቸው ቁልፍ ጉዳዮች ላይ በስፋት ተመካክረዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄይሉ ኡመር (ዶክተር) ዩኒቨርሲቲው ዘመናዊ ትምህርትን ይበልጥ ለማስፋፋት ከማዕከሉ ጋር ጠንካራ የትብብር አጋርነት ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር-ማስተማር፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎትን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በማንሳት፣ "ሥርዓተ ትምህርታችንን ወደ ዲጂታል የተቀናጀ መድረክ ለማሸጋገር እንፈልጋለን" ሲሉ የዩኒቨርሲቲውን ትልቅ ራዕይ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል የቻይና ብሔራዊ የትምህርት ቴክኖሎጂ ማዕከል (NCET) ምክትል ዳይሬክተር እና የልዑካን ቡድኑ ኃላፊ ሚስተር ዣኦ ዢያንዚ በበኩላቸው፣ በቻይና የትምህርት ሚኒስቴር ብሔራዊ የትምህርት ሀብቶች ማዕከል እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መካከል የሚፈጠረው ግንኙነትና ትብብር በትምህርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
What's Your Reaction?