የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚኒሶታ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል የፕላቲኒየም ስፖንሰር ሆነ
የሀገራችን አንጋፋና ግዙፉ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በሰሜን አሜሪካ ለሚካሄደው 43ኛው ዓመታዊ የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ከፍተኛው የድጋፍ ደረጃ የሆነውን የፕላቲኒየም ስፖንሰርሺፕ ስምምነት በይፋ ተፈራርሟል።
የሀገራችን አንጋፋና ግዙፉ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በሰሜን አሜሪካ ለሚካሄደው 43ኛው ዓመታዊ የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ከፍተኛው የድጋፍ ደረጃ የሆነውን የፕላቲኒየም ስፖንሰርሺፕ ስምምነት በይፋ ተፈራርሟል።
ይህ በስደት የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በስፖርትና በባህል የሚያገናኘው ታላቅ በዓል፣ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሰኔ 27 እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2026 (ከሰኔ 20 እስከ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም) በሚኒሶታ በሚገኘው በታዋቂው ቲሲኦ ስታዲየም በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህንን ውሳኔ የወሰደው በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራው ማህበረሰብ) ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር እና ለሀገራዊ ባህልና አንድነት ያለውን አጋርነት ለማሳየት ሲሆን፣ በፌስቲቫሉ ወቅትም የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶቹንና አዳዲስ አሰራሮቹን ለታዳሚው በስፋት ያስተዋውቃል ተብሎ ይጠበቃል።
What's Your Reaction?