የ40/60 እና የካፒታል ፕሮጀክት የንግድ ቤቶች ውል ማጠናቀቂያ ጊዜ ተራዘመ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ8ኛ ዙር (40/60) እና በ2ኛ ዙር (ካፒታል ፕሮጀክት) የንግድ ቤቶች ግልጽ ጨረታ አንደኛ ለወጡ አሸናፊዎች የነበረውን የውል ማፈጸሚያ ጊዜ ለተጨማሪ 5 ተከታይ የሥራ ቀናት ማራዘሙን አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ8ኛ ዙር (40/60) እና በ2ኛ ዙር (ካፒታል ፕሮጀክት) የንግድ ቤቶች ግልጽ ጨረታ አንደኛ ለወጡ አሸናፊዎች የነበረውን የውል ማፈጸሚያ ጊዜ ለተጨማሪ 5 ተከታይ የሥራ ቀናት ማራዘሙን አስታወቀ።
በሂደቱ ላይ የቴክኒክ መስተጓጎል በመፈጠሩ፣ ከተጫራቾች የገንዘብ ዝውውር ጋር የተያያዙ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግና፣ የባከኑ የሥራ ቀናትን ለመተካት እንደሆነ ተገልጿል።
አዲሱ የውል ማስፈጸሚያ ጊዜ ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ይሆናል ።
ስለሆነም አሸናፊዎች ቀደም ሲል በተገለጸው ቦታ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት ቀርበው፣ የሚጠበቅባቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች በማሟላት በዚህ በተጠቀሰው አጭር ጊዜ ውስጥ ውል እንዲፈጽሙ የኮርፖሬሽኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጥሪ አቅርቧል።
What's Your Reaction?