የኢቦላ ወርሽኝ ስርጭት በኮንጎ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 72 አዳዲስ ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ ከፍተኛው የቀን ስርጭት የተመዘገበ ሲሆን፣ ወረርሽኙ ወደ ሁለት ተጨማሪ የጤና ዞኖች ተዛምቶ በአጠቃላይ በሶስት ግዛቶች ውስጥ 31 ዞኖችን አዳርሷል። 

Jun 16, 2026 - 11:06
 0  4
የኢቦላ ወርሽኝ ስርጭት በኮንጎ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 72 አዳዲስ ሰዎች በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ ከፍተኛው የቀን ስርጭት የተመዘገበ ሲሆን፣ ወረርሽኙ ወደ ሁለት ተጨማሪ የጤና ዞኖች ተዛምቶ በአጠቃላይ በሶስት ግዛቶች ውስጥ 31 ዞኖችን አዳርሷል። 

ከግንቦት 15  የቡንዲቡግዮ ዝርያ ወረርሽኝ ወዲህ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 782 የደረሰ ሲሆን፣ የወረርሽኙ ዋና ማዕከል በሆነችው ኢቱሪ ግዛት ውስጥ አዳዲስ ተጠቂዎች የተገኙት በንቁ የማህበረሰብ ክትትልና በህዝብ ጥቆማ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የሟቾች ቁጥር በ29 ጨምሮ 181 ሲደርስ 40 ሰዎች ደግሞ ማገገማቸው ተገልጿል። ሆኖም ግን እንደ ጤና ባለስልጣናት ገለፃ የ21.5 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ክፍተት፣ የህክምና ማዕከላት አቅም ማነስ፣ ደካማ የንክኪ ክትትል እና የቁሳቁስ እጥረት ዋነኛ ተግዳሮቶች መሆናቸውን ተጠቁሟል።

 የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዣን ካሴያ በበኩላቸው በቴክኒክ እውቀት፣ በላብራቶሪ ድጋፍ እና በማህበረሰብ ተሳትፎ ምላሽ ለመስጠት እየሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ስርጭቱ እስኪቆም ድረስ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉና አጋር አካላትም ህይወትን ለመታደግ በአስቸኳይ ሀብት እንዲያሰባስቡ ጥሪ አቅርበዋል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow