ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል አዲስ የአሠራር ሥርዓት ተዘረጋ።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ እንዲከናወን መወሰኑን አስታውቋል።

May 12, 2026 - 13:22
 0  1
ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል አዲስ የአሠራር ሥርዓት ተዘረጋ።

የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል አዲስ የአሠራር ሥርዓት ተዘረጋ።

​የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ እንዲከናወን መወሰኑን አስታውቋል።

​የሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ይህ አዲስ አሠራር በዋናነት ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል ያለመ ነው።

​የአዲሱ አሠራር ዋና ዋና ነጥቦች፡-

#​የህትመት ማዕከል፡- ከዚህ ቀደም ተቋማት በየራሳቸው በጨረታ በሚያሸንፉ ድርጅቶች አማካኝነት የሚያሳትሙት አሠራር ለሐሰተኛ ሰነዶች ተጋላጭ በመሆኑ፣ ከእንግዲህ ሁሉም የመንግሥትና የግል ተቋማት ዲግሪዎች በአንድ ማዕከል ብቻ ይታተማሉ።

# ​የደህንነት መለያዎች፡-የሚታተሙት ሰርተፊኬቶች ልዩ መለያ ኮድ (QR Code)፣ ሴሪያል ቁጥር እና ሌሎች ዘመናዊ የደህንነት መጠበቂያዎችን ያካተቱ ይሆናሉ።

#​ተፈጻሚነት፡- አሠራሩ የ2017 ዓ.ም ተመራቂዎችን እና ከዚያ በፊት ተመርቀው ዲግሪያቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎችን በሙሉ ይመለከታል።

# ​ጊዜያዊ ማስረጃ፡- በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ (Temporary Degree) አሰጣጥ እንደነበረ ይቀጥላል።

#​የሽግግር ወቅት ድጋፍ፡-አዲሱ ዲግሪ ታትሞ እስኪደርስ ድረስ ለሚቸገሩ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚጽፍ ተገልጿል።

​በአሁኑ ወቅት ከ160 በላይ በሚሆኑ የፌዴራል ተቋማት ላይ የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ስራ እየተከናወነ ሲሆን፣ በቀጣይም በክልል እና በግል ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow