በትግራይ ትምህርት ቤቶች ከታቀደው አንድ ወር ጊዜ ቀደም ብለው ግንቦት 30 ሊዘጉ ነው
በትግራይ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከታቀደው ጊዜ አንድ ወር ቀደም ብለው፣ በመጪው ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚዘጉ ተሰማ።
በትግራይ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከታቀደው ጊዜ አንድ ወር ቀደም ብለው፣ በመጪው ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚዘጉ ተሰማ። ላለማቋረጥ ጥረት ቢደረግም፣ ከበጀት እና ከሎጂስቲክስ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች ሂደቱን አስገዳጅ አድርገውታል።
ትምህርት ቤቶቹ ቀድመው እንዲዘጉ ያደረጉት 3 ዋና ምክንያቶች:-
የደመወዝ መዘግየት እና የመምህራን መልቀቅ፦ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉሽ እንደገለጹት፤ ከፌደራል መንግሥት የበጀት ድልድል ጋር በተያያዘ የመምህራን ደመወዝ በወቅቱ መክፈል አልተቻለም። በዚህም ምክንያት መምህራን ሥራቸውን እየለቀቁ በመውጣታቸው የትምህርት ሂደቱ ተስተጓጉሏል።
የነዳጅ እጥረት፦ የነዳጅ አቅርቦት መከልከሉ ወይም መስተጓጎሉ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለማድረስ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። ይህም የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የግል ትምህርት ቤቶችም አብረው እንዲዘጉ ምክንያት ሆኗል።
የመሠረተ ልማት መቋረጥ፦ በአጠቃላይ በትምህርት መሠረተ ልማቶች ላይ ያጋጠሙ እክሎች ክልሉ ይህንን ውሳኔ እንዲያሳልፍ አስገድደውታል።
ሆኖም ግን ትምህርት ቤቶቹ ቀድመው የተዘጉ ቢሆንም፣ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ማጠቃለያ ፈተና ግን አይስተጓጎልም። በትግራይ ክልል የሚገረሙ ተማሪዎች ልክ እንደሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ሁሉ በተመሳሳይ ቀን ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተረጋግጧል።
What's Your Reaction?