በአዲስ አበባ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለመዘርጋት ስራዎች እየተከናወኑ ነው
በመጪው ክረምት አስተማማኝና ጥራት ያለው የኃይል አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ ሲባል እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በዕቅድ የሚደረግ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
በመጪው ክረምት አስተማማኝና ጥራት ያለው የኃይል አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ ሲባል እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በዕቅድ የሚደረግ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
በአገልግሎቱ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ገበየሁ ሊካሳ እንደገለጹት፣ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር አስቀድሞ ለመከላከል ሰፋፊ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ያለውን 4ኛውን ምዕራፍ የመልሶ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ሲባል ከመጋቢት ወር ጀምሮ የኃይል መቆራረጡ ከፍ ማለቱ ተዘግቧል።
አብዛኛው የዲስትሪቢዩሽን መስመር ረጅም ጊዜ ያገለገለ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለመልሶ ግንባታው ከፍተኛ የፋይናንስ አቅምና ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ በዕቅድ የሚቋረጥ የኃይል ድግግሞሽ ሊበዛ የቻለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እነዚህን የፕሮጀክት ስራዎች ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
What's Your Reaction?