በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጭቃ ቤት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ታገደ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ከተሞችን ለማዘመን እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተጣጣመ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት አዲስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ከተሞችን ለማዘመን እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተጣጣመ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት አዲስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል።
በዚህም መሠረት መመሪያው ከወጣበት (ደብዳቤው ከደረሰበት) ቀን ጀምሮ በማንኛውም ማዘጋጃ ቤት በኩል የጭቃ ቤት ግንባታ ፈቃድ ማጽደቅ ሙሉ በሙሉ መታገዱ ታውቋል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን
በእንጨትና ጭቃ ግንባታ ሳቢያ የሚመጣውን የደን መመናመን ለመግታት።
የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የድርቅና የጎርፍ አደጋ ለመከላከል ::
ከእንግዲህ በኋላ ማንኛውም ግንባታ ከተማን በሚያዘምኑና ደረጃቸውን በጠበቁ ግብዓቶች ማለትም በብሎኬት፣ በጡብ እና በተሻሻሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቻ መከናወን እንዳለበት ታዟል።
ይህ አዲስ መመሪያ በአሁኑ ወቅት ተፈፃሚ መሆን የጀመረው በአንድ ክልል (በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል) ቢሆንም፣ በቀጣይ ግን በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እንደሚተገበር ተነግሯል።
What's Your Reaction?