ታላቁ የእግር ኳስ መድረክ የዓለም ዋንጫ
ታላቁ የእግር ኳስ መድረክ የዓለም ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እየመጣ የተለያዩ የማይረሳ ክስተት ትቶ ያልፋል።
ታላቁ የእግር ኳስ መድረክ የዓለም ዋንጫ በየአራት ዓመቱ እየመጣ የተለያዩ የማይረሳ ክስተት ትቶ ያልፋል።
አስካሁን በተካሄዱት የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ታሪክ ጋር በተያያዘ እነ ጋሪ ሊኒከር፣ አለን ሺረር እና ሚካህ ሪካርድስ ቢቢሲ ላይ ደረጃዎችን አውጥተዋል
1.ብራዚል - 1970
2.እንግሊዝ - 1966
3. ብራዚል - 2002
4.አርጀንቲና - 1986
5. ፈረንሳይ - 1998
6.ምዕራብ ጀመርን - 1990
7. ስፔን - 2010
8. ጣልያን - 1982
9. ፈረንሳይ - 2018
10.አርጀንቲና - 1978 ናቸው።
እንግዲህ የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1930 በኡራጓይ ሀገር ሲሆን፣ በየ4 ዓመቱ ይካሄዳል። ነገር ግን በታሪክ አጋጣሚ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት በ1942 እና 1946 ዓመታት ውድድሩ አልተካሄደም።ዓለም ዋንጫን በብዛት ያነሱ ሀገራት እና ያሸነፉባቸው ዓመታት
ብራዚል (5 ጊዜ)፦ 1958፣ 1962፣ 1970፣ 1994 እና 2002
ጀርመን (4 ጊዜ)፦ 1954፣ 1974፣ 1990 (እንደ ምዕራብ ጀርመን) እና 2014
ኢጣሊያ (4 ጊዜ)፦ 1934፣ 1938፣ 1982 እና 2006
አርጀንቲና (3 ጊዜ)፦ 1978፣ 1986 እና 2022
ፈረንሳይ (2 ጊዜ)፦ 1998 እና 2018
ኡራጓይ (2 ጊዜ)፦ 1930 እና 1950
እንግሊዝ (1 ጊዜ)፦ 1966
ስፔን (1 ጊዜ)፦ 2010
በ1930 የጀመረው የአለም ዋንጫ እግር ኳስ 2026 ላይ ደርሷል። ሌሎች እነዚህን መሰል ስፖርታዊ መረጃዎችበየቀኑ ወደ እናንተ እናደርሳለን። መረጃዎቹ ወደ እናንተ እንዲደ ርሱ የሎሚ ኒውስን ገፅ ፎሎ እያደረጋችሁ ቤተሰብ ሁኑ
What's Your Reaction?