የ2019 በጀት ዓመት የ2.34 ትሪሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለምክር ቤት ተላከ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ ከአንድ ወር በኋላ ለሚጀምረው የ2019 በጀት ዓመት የተዘጋጀውን የ2.34 ትሪሊዮን ብር ረቂቅ የፌደራል መንግስት በጀት መርምሮ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላልፏል።

Jun 9, 2026 - 15:52
 0  6
የ2019 በጀት ዓመት የ2.34 ትሪሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለምክር ቤት ተላከ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ ከአንድ ወር በኋላ ለሚጀምረው የ2019 በጀት ዓመት የተዘጋጀውን የ2.34 ትሪሊዮን ብር ረቂቅ የፌደራል መንግስት በጀት መርምሮ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላልፏል።

ካለፈው ዓመት የ1.93 ትሪሊዮን ብር በጀት ጋር ሲነጻጸር በ410 ቢሊዮን ብር ገደማ (ወደ ግማሽ ትሪሊዮን ብር ጠጋ የሚል) ጭማሪ ያሳየው ይህ ግዙፍ በጀት፣ በሀገሪቱ የረጅም ጊዜ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊሲካል ማዕቀፍ (ከ2019 እስከ 2023 ዓ.ም) ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ነው።

ረቂቅ በጀቱ የመንግስትን መደበኛና ካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች የሚደረጉ ድጋፎችን እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የሚውሉ የፋይናንስ አቅርቦቶችን ያካተተ ሲሆን፤ በያዝነው የ2018 በጀት ዓመት ለመደበኛ ወጪ 1.2 ትሪሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች ደግሞ 415 ቢሊዮን ብር ተመድቦ እንደነበር ይታወሳል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow