የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ፊፋ (FIFA) በደጋፊዎች ላይ ያልተጠበቀና አስደናቂ እገዳ ጥሏል

ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ሲገቡ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉ የውሃ መያዣዎችን ይዘው እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ ተከልክለዋል።

Jun 5, 2026 - 10:35
 0  8
የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ፊፋ (FIFA) በደጋፊዎች ላይ ያልተጠበቀና አስደናቂ እገዳ ጥሏል

ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ሲገቡ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉ የውሃ መያዣዎችን ይዘው እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ ተከልክለዋል።
ከዚህ በፊት ባዶ የሆኑ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ይዞ መግባት እንደሚቻል ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ፣ ፊፋ በድንገት ህጉን ቀይሮታል።

ፊፋ ውሳኔውን ያስተላለፈው ለደህንነት ሲባል እንደሆነ ገልጿል። በደጋፊዎች፣ በተጫዋቾች እና በዳኞች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ማናቸውንም የሚወረወሩ ነገሮችን (ጠርሙስ፣ ኩባያ) ለመከላከል ሲባል ነው ብሏል።

ይህ ውሳኔ በተለይ የሙቀት መጠኑ ከ26 - 28 ዲግሪ ሴኒቲግሬድ በሚደርስባቸው ስታዲየሞች ውስጥ ለሚታደሙ ደጋፊዎች ትልቅ ስጋት ፈጥሯል።
የእንግሊዝ ደጋፊዎች ማህበር በቁጣ ባወጣው መግለጫ፡-"ቀጣዩ እገዳ ምንድነው? የፀሐይ መከላከያ ክሬም ከልክለው በስታዲየም ውስጥ እንድንገዛ ሊያደርጉን ነው? ይህ ግልጽ የሆነ የገንዘብ ብዝበዛ ይመስላል!"በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ፊፋ በበኩሉ ደጋፊዎች በሙቀት እንዳይጎዱ የውሃ መርጫዎች፣ ማቀዝቀዣዎች እና ድንኳኖች በስታዲየሙ ዙሪያ እንደሚያዘጋጅ ቃል ገብቷል። ነገር ግን በስታዲየም ውስጥ የሚሸጠው የውሃ ዋጋ ከተለመደው የስታዲየም ዋጋ ጋር እኩል እንደሚሆን ገልጿል።
የዘንድሮው 48 ሀገራት የሚሳተፉበት የአለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ሀገራት (አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ) አስተናጋጅነት ከሰኔ 4 እስከ ሐምሌ 12 ይካሄዳል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow