የምስራቃዊ የፍልሰት መስመር እና የኢትዮጵያውያን የሞት ቀጠና

​ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ይፋ ባደረገው አስደንጋጭ ሪፖርት መሠረት፣ እ.ኤ.አ 2025 በአፍሪካ ቀንድ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ የሞት አደጋ የተመዘገበበት ጥቁር ዓመት ሆኖ አልፏል።

May 13, 2026 - 10:59
 0  3
የምስራቃዊ የፍልሰት መስመር እና የኢትዮጵያውያን የሞት ቀጠና

የምስራቃዊ የፍልሰት መስመር እና የኢትዮጵያውያን የሞት ቀጠና

​ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ይፋ ባደረገው አስደንጋጭ ሪፖርት መሠረት፣ እ.ኤ.አ 2025 በአፍሪካ ቀንድ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ የሞት አደጋ የተመዘገበበት ጥቁር ዓመት ሆኖ አልፏል። በተለይም "ምስራቃዊ የጉዞ መስመር" ተብሎ በሚጠራውና በጂቡቲና የመን በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ በሚያመራው አደገኛ መንገድ ላይ ካለቁ 922 ስደተኞች መካከል 700 ያህሉ (ከ76% በላይ) ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የስደቱን አስከፊነት ገፅታ በግልጽ ያሳያል።
​የመንገዱ ርዝመት፣ በባሕር ላይ የሚከሰቱ የጀልባዎች መገልበጥ እንዲሁም በየመንና በሳዑዲ ድንበር አካባቢ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ለዜጎቻችን እልቂት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው። በሀገር ውስጥ ያለው ግጭት፣ የኢኮኖሚ ቀውስና የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው ድርቅ ዜጎችን ለዚህ አደገኛ አማራጭ ቢገፋፋቸውም፣ ሕጋዊ የፍልሰት መንገዶች አለመኖርና የደላሎች ሴራ ስደቱን ወደማይመለሱበት የሞት ጉዞ ቀይሮታል። ይህ ሪፖርት ስደት መፍትሔ ከመሆን ይልቅ የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ የሚጠፋበት የሲኦል መንገድ እየሆነ መምጣቱን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዳግም አሳይቷል።

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow