የጋምቤላው ‘ሺያ ቅቤ’ ከባህላዊ አሰራር ወደ ዓለም አቀፍ ብራንድነት!

በኮስሞቲክስ እና በምግብ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ "አረንጓዴ ወርቅ" ተብሎ የሚጠራው የሺያ ቅቤ (Shea Butter)፣ የጋምቤላ ክልል አዲስ የኢኮኖሚ መተንፈሻ ሊሆን ነው። የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ተፈጥሯዊ ሀብት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሊያደርገው የሚችል የምርምር ሥራ መጀመሩን አብስሯ

May 13, 2026 - 10:39
 0  2
የጋምቤላው ‘ሺያ ቅቤ’ ከባህላዊ አሰራር ወደ ዓለም አቀፍ ብራንድነት!

የጋምቤላውሺያ ቅቤከባህላዊ አሰራር ወደ ዓለም አቀፍ ብራንድነት!

በኮስሞቲክስ እና በምግብ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ "አረንጓዴ ወርቅ" ተብሎ የሚጠራው የሺያ ቅቤ (Shea Butter) የጋምቤላ ክልል አዲስ የኢኮኖሚ መተንፈሻ ሊሆን ነው። የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ተፈጥሯዊ ሀብት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሊያደርገው የሚችል የምርምር ሥራ መጀመሩን አብስሯል።

 ምንም እንኳን የሺያ ዛፍ በኢትዮጵያ በጋምቤላ ክልል ብቻ በስፋት የሚገኝ ቢሆንም፣ ማህበረሰቡ እስካሁን ሲጠቀምበት የቆየው እጅግ አድካሚ በሆነ ባህላዊ ዘዴ ነበር። ይህንን ለመቀየር ዩኒቨርሲቲው ባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ እየሰራ ይገኛል። ምርቱን የጋምቤላ ክልል የንግድ ምልክት በማድረግ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ታቅዷል።እስካሁን የተከናወኑ የላብራቶሪ ምርምሮች ተስፋ ሰጪ ውጤት አሳይተዋል።የሺያ ቅቤ ለውበት መጠበቂያ ምርቶች (Cosmetics) እንዲሁም ለቸኮሌትና ለኬክ ዝግጅት ከፍተኛ ግብዓት በመሆኑ የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት ትልቅ አቅም አለው።

የምርምር ሥራው ምርትን ከማሳደግ ባለፈ፣ የሺያ ዛፎች እንዳይጠፉ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በጎንዮሽ እያከናወነ ይገኛል።የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ድሪባ ኢቲቻ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮ ሀብቱን ወደ ኢኮኖሚ ጥቅም ለመቀየር በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል።

ስለ ጋምቤላ የሺያ ቅቤ ምርት ምን ያውቃሉ? ሀሳብዎን በኮሜንት ያጋሩን!

#MEA #Gambella #SheaButter #Ethiopia #Innovation #Agriculture #EconomicGrowth

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow