የኢትዮጵያየብድር ሽግሽግ ድርድር እና የፋይናንስ ሚኒስቴር ይፋዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የቦንድ አበዳሪዎች ጋር የተደረገው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሽግሽግ ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ተገለጠ
የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የቦንድ ባለቤቶች (Eurobond Holders) ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንታት (ከግንቦት 6 እስከ ግንቦት 27 ቀን) ሲያካሂድ የነበረው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሽግሽግ (Debt Restructuring) ድርድር ያለ ስምምነት መጠናቀቁን በይፋ አስታወቀ።
መንግስት ባለፈው ጥር ወር ላይ ከአበዳሪዎች ጋር “በመርህ ደረጃ” ላይ ደርሶበት የነበረው ስምምነት፣ በፓሪስ ክለብ እና በባለብዙ ወገን አበዳሪዎች ስብስብ (Official Creditor Committee - OCC) ውድቅ መደረጉ ይታወሳል። የኦሲሲ (OCC) ኮሚቴ ስምምነቱን ውድቅ ያደረገው “ሁሉንም አበዳሪዎች በእኩልነት የማስተናገድ” (Comparability of Treatment) መርህን አይከተልም በሚል ነበር።
What's Your Reaction?