ዴቪድ ራያ የአርሰናል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተባለ!
የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በታላቅ ድምቀት ያነሳው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል፣ የውድድር ዓመቱን የማጠቃለያ ወር ምርጥ ተጨዋቹን ይፋ አድርጓል።
የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በታላቅ ድምቀት ያነሳው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል፣ የውድድር ዓመቱን የማጠቃለያ ወር ምርጥ ተጨዋቹን ይፋ አድርጓል።
ስፓኒሻዊው የግብ ዘብ ዴቪድ ራያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።
በመጨረሻዎቹ ወሳኝ ጨዋታዎች ላይ ድንቅ ብቃቱን ያሳየውና ለክለቡ የዋንጫ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተው ራያ፣ ይህንን ክብር ሲቀዳጅ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
መድፈኞቹ የፕሪሚየር ሊጉን አሸናፊነት ባረጋገጡበት በዚህ ታሪካዊ ወር፣ የዴቪድ ራያ በአስደናቂ ብቃት መቅረብና ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት (Clean Sheets) ለሽልማቱ በዋናነት እንዳጨው ተገልጿል።
#
ሱማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታን ከአሜሪካ ወደ ቱርክ እንዲመለሱ ተደረገ
ታዋቂው ሱማሊያዊ የእግር ኳስ ዳኛ ኦማር አርታን ለዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከአፍሪካ ከተመረጡ እጩዎች መካከል አንዱ የነበሩ ቢሆንም፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከአሜሪካ ወደ ቱርክ እንዲመለሱ መደረጉ ተሰምቷል።
ዳኛው በቪዛ መዘግየት ምክንያት ጉዟቸው ተስተጓጉሎ የነበረ ቢሆንም፣ ከኬንያ ተነስተው በቱርክ አድርገው ትራንዚት በመጠቀም አሜሪካ መድረስ ችለው ነበር። ነገር ግን፣ አሜሪካ ከገቡ በኋላ ከአሜሪካ መንግስት በኩል በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ወደ ቱርክ እንዲመለሱ ተደርገዋል።
What's Your Reaction?